የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በዜግነት ዘርፍ ወደ  ተቋሙ ለተቀላቀሉ 280 አዲስ ሰራተኞች ስልጠና እየሰጠ እንደሆነ ተገለፀ።

አዲስ አበባ: ግንቦት 26/2017 ዓ.ም

የኢሚግሬሽና ዜግነት አገልግሎት በዜግነት ዘርፍ ወደ  ተቋሙ ለተቀላቀሉ 280 አዲስ ሰራተኞች በተለያዮ ርዕሶች ላይ ለ5 ቀናት የሚቆይ ስልጠና እየተሰጠ እንደሆነ ተገልፆል።

በስልጠና መድረኩ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ቢቂላ መዝገቡ: ተቋሙ አገራዊ ለውጡን ተከትሎ ካለፈው ዓመት ጀምሮ 11 የሪፎርም አጀንዳዎችን በመቅረፅ  እየተገበረ መሆኑን ገልፀው ከዚህ ውስጥም የሰው ሀይልና አስተዳደር አንዱ መሆኑን ተናግረዋል።

ሰልጣኞች በሁሉም መንገድ ራሳችሁን ማዘጋጀት እና በስነ-ምግባር ማነፅ ይጠበቅባችኋል ያሉት ም/ዋ/ ዳይሬክተሩ የተጀመረው ሪፎርም መስመር ከያዘ በኋላ መሰረቱን በምናፀናበት ሰአት ወደ ተቋማችን በመምጣታችሁ  እድለኛ ናችሁ ብለዋል።

በመጨረሻም  ዛሬ ከእናንተ የሚጠበቅ ለመማር ዝግጁ መሆን እና ለማገልገል ቅን መሆን ሲሆን በቀጣይ በሚሰጡ ስልጠናዎች አቅማችሁን በማሳደግ በተመደባችሁበት ቦታ ሁሉ ሀገራችሁን በታማኝነት እንድታገለግሉ አደራ እላለሁ ብለዋል።

 የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት