የኢሚግሬሽንና ዜግነት አግልግሎት በኢሚግሬሽን ዘርፍ ከቻይና ጋር ያለውን ትብብር አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገለፀ።

አዲስ አበባ፡ ጳጉሜ 3/2017ዓ.ም

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ከፍተኛ አመራሮች ከቻይና ኤምባሲ ልዑካን ቡድን ጋር ውይይት አድርገዋል። የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት ተቋሙ ባለፋት ሁለት አመታት ባከናወነው የሪፎርም ስራ  ቻይና ከፍተኛ ትብብር ማድረጓን ገልፀው ምስጋና አቅርበዋል። 

የኢትዮጵያ እና ቻይና ግኑኝነት በርካታ አመታት ያስቆጠረ መሆኑን የጠቀሱት ወይዘሮ ሰላማዊት በአሁኑ ወቅትም ለቢዝነስ፥ ኢንቨስትመንት፥ ለቱሪዝም እና ሌሎች ጉዳዮች ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ ቻይናውያን ቁጥር ከፍተኛ ነው ብለዋል። 

ቻይናውያን በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከቪዛ እና ሌሎች የተቋሙ አገልግሎት ጋር ተያይዞ ምንም አይነት ችግር እንዳይገጥማቸው በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል፤ በቀጣይም ይህ ግንኙነት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ጠቅሰዋል። 

የቻይና ኤምባሲ ልዑክ መሪ ሱን ሚንግሺ በበኩላቸው ኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በቆራጥ አመራርነት ተቋሙን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደገፈና ዲጅታላይዝ ለማድረግ የተሰራውን የሪፎርም ስራ አድንቀዋል። ተቋሙ ቻይናውያን እና ለሌሎች የውጭ ዜጎች ከቦሌ አየር መንገድ ጀምሮ ሁሉም የውጭ ዜጎች አገልግሎት ቦታዎች ፈጣንና ቀልጣፋ መሆን መደነቃቸውንም ነው የገለፁት።

በቀጣይ ቻይና ለተቋሙ በቴክኒካል መሳሪያዎች ድጋፍ እንደምታደርግና   ስልጠና እና የትምህርት እድል በመስጠት በሰው ሃይል የአቅም ግንባታ እንዲሁም የተቋሙ የሪፎርም ስራዎች ላይ ያለውን ትብብርና ወዳጅነት አጠናክራ እንደምትቀጥል ገልፀዋል።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት

Latest Posts

Any Questions?

Call us!

8133