አዲስ አበባ፡ ጳጉሜ 5/2017 ዓ.ም
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አግልግሎት የአዲስ አመት በዓልን ምክንያት በማድረግ የማዕድ ማጋራት መርሀ ግብር ያከናወነው ጎተራ በሚገኘው የተቋሙ ዋና ቢሮ ነው።
ተቋሙ ከ1 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ነው የማእድ ማጋራቱን ያከናወነው።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት በመርሀ ግብሩ ላይ በመገኘት ለአዲስ አመት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈው፣ ተቋሙ ከተሰጠው ሀገራዊ ተልእኮ ጎን ለጎን በተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራዎች ላይ በመሳተፍ ላይ ይገኛል ብለዋል።
ለአብነትም በመጠናቀቅ ላይ ባለው የ2017ዓ.ም በደም ልገሳ ፥ ችግኝ ተከላ ፥ የትምህርት ቁሳቁሶች ድጋፍ እና መሰል የበጎ አድራጎት ስራዎች ላይ መሳተፋን አስታውሰዋል።በየዓመቱ በርካታ በጀት በመመደብ የማህበራዊ ኃላፊነት ሥራዎችን እንደሚያከናውን የገለፁት ወይዘሮ ሰላማዊት በዛሬው እለትም ከ 1 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ለተውጣጡ ድጋፍ የሚሹ ወገኖች የማእድ ማጋራት መደረጉን ገልፀዋል።።
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ዘመን ተስፋዬ የኢሚግሬሽንንና ዜግነት አግልግሎት እያደረገ ያለው የመተሳሰብ፥ የመረዳዳት እና መሰል ሰው ተኮር የበጎ አድራጎት ስራዎች ማኅበራዊ ኃላፊነትን በመወጣት ረገድ ለሌሎች ተቋማት ምሳሌ መሆኑን የሚያሳይ ነው ያሉት። በቀጣይም ይህንኑ ሥራውን አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል፡፡
የማዕድ ማጋራቱ መርሀ ግብር ተጠቃሚዎች ኢሚግሬሽንና ዜግነት አግልግሎት ላደረገላቸው ድጋፍ አመስግነው ሌሎች ተቋማትም የተቋሙን አርዓያነት ያለው ተግባር እንዲከተሉ ጠይቀዋል፡፡
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
