የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ለደንበኞች የሚሰጠውን አገልግሎት ፈጣን ለማድረግ እየተሰራ ያለውን የኦንላይን ፖርታል ሲስተም ገመገመ።

አዲስ አበባ: መስከረም 01/2018 ዓ.ም

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት  እና የአገልግሎቱ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ቶፖን ኩባንያ እያበለፀገ ያለውን አዲሱ  የኦንላይን ፖርታል ሲስተም ገምግሟል። 

በቶፓን ኩባንያ እያበለፀገ ያለው አዲስ ሲስተም የፓስፖርት፣ የትውልደ ኢትዮጵያ መታወቂያ ፥ የቪዛ እና ሌሎች በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር የሚሰጡ የተቋሙ አገልግሎቶችን አስተማማኝ፥ ምቹ እና ዘመናዊ እንዲሆኑ ያስችላል ተብሏል። 

በግምገማው ወቅት በተቋሙ የስራ ኃላፊዎች ሲስተሙ ደህንነቱ የተጠበቀ እና አስተማማኝ እንዲሆን የሚያስችል ግብአት የተሰጠ ሲሆን በግብአቱ መሰረት ማሻሻያ ሊደረግበት እንደሚገባ አቅጣጫ ተሰጥቷል።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አገሪቷ የያዘችውን 2025 ዲጅታል ዕቅድ መሠረት በማድረግ ከዘመኑ ጋር የሚሄድ የዲጂታል ሲስተም ስራ ላይ ማዋልን ከ11 የተቋሙ የሪፎርም አጀንዳዎች አንዱ  አድርጎ እየሰራ መሆኑ ይታወቃል።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት

Latest Posts

Any Questions?

Call us!

8133