የኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር አ.ማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢንጂነር ታከለ ኡማ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አግልግሎትን  ጎበኙ

አዲስ አበባ፡ መስከረም 05/2018 ዓ.ም

 የኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በተቋሙ በመገኘት በቴክኖሎጅ በመታገዝ እያከናወነ ያለውን የፓስፓርትን ጨምሮ የጉዞ እና የይለፍ ሰነድ ዝግጅት፣ ፕርሰናላይዜሽን እና የህትመት የአገልግሎት ማእከላት ያለውን የስራ እንቅስቃሴ ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።

ተቋሙ የሰዉ ሃይል አቅምን ለማሳደግ፣ በቴክኖሎጂ የታገዘ ዘመናዊ አሰራር ለመዘርጋት  እንዲሁም ወቅቱን የዋጁ የአሰራር ስርዓቶች ትግበራ ዙሪያ የተቋሙ ምክትል ዋና ዳይሬክተር እና የዜግነት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ቢቂላ መዝገቡ እና የተቋሙ ምክትል ዋና ዳይሬክተር እና የኢሚግሬሽን ዘርፍ ኃላፊ ኢንጂነር ጎሳ ደምሴ ገለጻ አድርገውላቸዋል።   

ኢንጂነር ታከለ ኡማ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ከነበረበት ውስብስብ ችግር በመውጣት እና ስርነቀል ሪፎርም በማድረግ አገልግሎቱን በቴክኖሎጂዎች የታገዘ፥ ፈጣንና ቀልጣፋ ማድረጉን አድንቀዋል። 

ተቋሙ ደህንነቱ አስተማማኝ የሆነ የፓስፓርት ህትመትን በሀገር ውስጥ በማድረግ ለውጭ ምንዛሬ ይወጣ የነበረውን ወጪ ማስቀረት መቻሉ እንዲሁም አሰራሮችን ዲጅታላይዝ የማድረግ ስራ ሌላው የተቋሙ ስኬት በመሆኑ መደሰታቸውን ገልጸዋል። ይህ አይነቱ የሪፎርም ስራና የአመራር ቁርጠኝነት ለሌሎች ተቋማት አርአያ እንዲሆን ያስችለዋልም ብለዋል።  

 ኢንጂነር ታከለ አያይዘውም ተቋሙ  በከተማም በገጠርም የሚገኙ ዜጎች በአቅራቢያቸው አገልግሎት እንዲያገኙ እየሰራ ያለውን የተደራሽነት ስራም አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት

Latest Posts

Any Questions?

Call us!

8133