አዲስ አበባ፡ መስከረም 10/2018 ዓም
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በቅርቡ ግንባታቸዉ አዲስ አበባ ላይ በሚጀመሩ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የግንባታ ቅድመ ዝግጅት ዙሪያ ውይይት አካሂዷል።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት ተቋሙ የፓስፓርት ፈላጊውን ህብረተሰብ ቁጥር ታሳቢ በማድረግ አገልግሎቱን ለማስፋት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም በአዲስ አበባ አራት ተጨማሪ የአዳዲስ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ግንባታ ለመጀመር የቅድመ ዝግጅት ስራ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ተቋሙ የሚያከናውነው ቅርንጫፎችን የማስፋፋት ስራ ለአገልግሎት ፈላጊዎች በአቅራቢያቸው አገልግሎትን በመስጠት የወጪ ፥ ጊዜ እና ጉልበት እንደሚቀንስ የገለጹት ወይዘሮ ሰላማዊት ይህም ተቋሙን ደንበኞች የሚደሰቱበትና እርካታ የሚያገኙበት ተቋም የማድረግ የሪፎርም አካል መሆኑን ገልጸዋል።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
