18ኛው የብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ ቀን በኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት በደማቅ ሁኔታ ተከበረ።

አዲስ አበባ ፡ ጥቅምት 03 ቀን 2018 ዓ.ም 

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በአገር አቀፍ ደረጃ ለ18ኛ ጊዜ”ሰንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብስራት፣ ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉአላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ሕዳሴ” በሚል መሪ ቃል የአገልግሎቱ የስራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች በተገኙበት በኢትዮጵያ ብሔራዊ  ህዝብ መዝሙር ታጅቦ የሰንደቅ ዓላማ መስቀል ፕሮግራም ተከናውኗል፡፡ 

በፕሮግራሙ ሰንደቅ ዓላማ የአንድ አገር የማንነት መገለጫ መሆኑን የተወሳ ሲሆን አገራችን ኢትዮጵያም  በቀኝ ያልተገዛች የነፃነት ምሳሌ በመሆን ታሪኳ እና ሰንደቅ ዓላማ ለሌሎች ጭቁን ህዝቦች አርአያና ተምሳሌት ሆናለች ተብሏል፡፡

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት

Latest Posts

Any Questions?

Call us!

8133