የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ለዜጎች የሚሰጠውን አገልግሎት ጥራት እና ተደራሽነት መሻሻል ለሌሎች ተቋማት ምሳሌ የሚሆን ነው ሲሉ የኢፌድሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስትር ክብርት ዶክተር መቅደስ ዳባ ገለፁ።

አዲስ አበባ ፡ ጥቅምት 06/2018 ዓ.ም

የኢፌድሪ ጤና ጥበቃ ሚኒስትር ክብርት ዶክተር መቅደስ ዳባ ጎተራ በሚገኘው የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና መስሪያ ቤት በመገኘት የፓስፖርት ህትመት፥ ስርጭት እና እደላ ማዕከል፥ የቪዛ አገልግሎት፥ 8133 ነፃ የጥሪ ማዕከልን ጨምሮ ሌሎች በተቋሙ እየተሰጡ ያሉ አገልግሎቶችን ጎብኝተዋል።  

የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት እንዲሁም የአገልግሎቱ ም/ዋና ዳይሬክተርና የኢሚግሬሽን ዘርፍ ኃላፊ አቶ ጎሳ ደምሴ እና የተቋሙ ም/ዋና ዳይሬክተርና የዜግነት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ቢቂላ መዝገቡ ተቋሙ የአገልግሎት አሰጣጥን ለማዘመን እና የተገልጋዩን ህብረተሰብ እርካታ እውን ለማድረግ ያከናወነውን ሪፎርም  የማስቀጠልና የማፅናት ተግባራት ዙሪያ ለክብርት ሚኒስትሯ ገለፃ አድርገውላቸዋል፡፡ 

የስራ ኃላፊዎቹ ተቋሙ ያከናወነውን ሪፎርም ተከትሎ  ዘመኑን በዋጀ ቴክኖሎጂ በመታገዝ ፓስፓርት፥ ቪዛ ፥ የትውልደ ኢትዮጵያ መታወቂያን ጨምሮ ሌሎች የይለፍና የጉዞ ሰነዶችን ደህንነቱና ጥራቱን ጠብቆ በሀገር ውስጥ ማምረት መቻሉን ፥ አሰራሩን ዲጅታላይዝ ማድረጉ፥ አዳዲስ ቅርንጫፎችን እና የአገልግሎት መስጫ መስኮቶችን ቁጥር በማሳደግ ተደራሽነትን ማሳደግ መቻሉን እና በሌሎች ዘርፎችም ተጨባጭ ለውጥ መምጣቱን ለክብርት ሚኒስትሯ ገልፀውላቸዋል።

ክብርት ሚንስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ ተቋሙ በቴክኖሎጂ በመታገዝ ዘመኑን የሚመጥን  አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን በጉብኝታቸው መመልከታቸውን ገልፀው ይህን መሰል ውጤት ተኮር የሪፎርም ስራ እንዲሁም የሰራተኛና የአመራር ቁርጠኝነት ሌሎች ተቋማት በአርያነት ሊከተሉት የሚገባ መሆኑን ተናግረዋል ፡፡ 

ኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት

Latest Posts

Any Questions?

Call us!

8133