የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ኢቢሲ ጋራ በጋራ በሚሰሩባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አደረጉ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር ፣ 9 ፣ 2018 ዓ.ም

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ከኢቢሲ ጋራ በጋራ በሚሰሩባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል፥ሀገራዊ ራዕይን የልማት ግቦችን ብሄራዊ ጥቅምን በማስጠበቅ ሂደት ላይ ሁለቱ ተቋማት በጋራ መስራት በሚቻልበት አስቻይ ሁኔታዎች ላይ ውይይት ያደረጉ ሲሆን በውይይቱ ላይ የሁለቱ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል ።

በአገልግሎት በተካሄደው ሰው ተኮር ሪፎርም የመጣው ለውጥ ፤ ዛሬ ላይ በከፍተኛ ደረጃ ሃገራዊ ሃላፊነትን ለመወጣት ያስቻለ መሆኑን የገለፁት የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት የዜጎች ፍላጎትን ፣ የመረጃ ክፍተት ለመሙላት ከኢቢሲ ጋራ መስራት ለተሟላ አገልግሎት እና ተደራሽነት አጋጅ መሆኑን ገልፀዋል ።

በኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ውሰጥ የመጣው ለውጥ የሚታይ ነው ፤በቴክኖሎጂ የታጀበ አዳዲስ አሰራርን የዘረጋ ቀላል የሚባል አይደለም በአጭር ግዜ ውስጥ ይህ ስኬት ያሉት የኢቢሲ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ቢንያም ኤሮ ኢቢሲ በቋንቋ ተደራሽነት እና በማህበራዊ ሚዲያ አማራጭ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ በጋራ እንሰራለን ብለዋል።

የመረጃ ክፍተቶችን እና የተዛቡ አስተሳሰቦች በቀጣይ በጋራ ሆኖ ለመቅረፍ እንደሚሰራ የገለፁት የኢቢሲ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ቢንያም ኤሮ የአገልግሎቱ ራዕይ በጋራ ስራ እናሳካለን ብለዋል ።

በውይይቱ ላይ የሁለቱ ተቋማት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል ።


የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት