አዲስ አበባ ፣ ህዳር 3 2018 ዓ.ም
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የበጀት አመቱን የጥቅምት ወር አፈፃፀም እና በአፈፃፀም ሂደት ላይ የታዩ ክፍተቶችን ያጋጠሙ ተግዳሮቶች የገመገመ ሲሆን ፥ ተቋማዊ የማስፈፀም አቅም ፣ ገቢን ማሳደግ የሃብት አጠቃቀምና የዜግነት አገልግሎትን የስራ አፈፃፀምን በጥልቀት ገምግሟል ።
ለተሻለ የስራ ጥራት እና በተሳካ ሁኔታ እቅድን ለመፈፀም እየተገናኙ ውይይት ማድረግ ስራዎችን መገምገም ለተሟላ የለውጥ ስራ አስፈላጊ መሆኑን የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት ገልፀዋል ።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የጥቅምት ወርን የስራ አፈፃፀም የገመገመ ሲሆን በግምገማው ወቅትም በጥቅምት ወር ብቻ ከ178ሺ በላይ የፓስፓርት አመልካቾች መሰጠቱ በ30 ቀናት ግምገማ ላይ ተገልጿል።
ለሀገር ውስጥ ስርጭት 169,880 የተዳረስ ሲሆን ከሀገር ውጪ ለሚኖሩ ዜጎች ደሞ 8,878 መሰራጨቱ የ30 ቀናት ግምገማ ላይ ተገልጿል ።
በገቢ ደረጃ በጥቅምት ወር 5 ቢልዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 3.7 ቢልዮን ብር ተሰብስቧል ይህም የእቅዱ 67.4% በመቶ የተሳካ ሲሆን ከሃምሌ እስከ ጥቅምት ባለው የግዜ ገደብ ውስጥ 16 ቢልዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 12.818 ቢልዮን ብር ተሰብስቧል በዚህም የእቅዱ 80% በመቶ መሳካቱን የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ ላይ ተገልጿል ።
ሰራተኞችን ለማብቃት የደንበኞችን ፍላጎት ለሟሟላት ተከታታይ ስልጠና መስጠት አስፈላጊ መሆኑ ታምኖበት ወደ ስራ ተገብቶ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣቱን በስራ አፈፃፀሙ ላይ ያነሱት የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት ለተሻለ ስራ በጋራ መስራት አስፈላጊ መሆኑን አስገንዝበዋል ።
የፓስፖርት ተደራሽነት ለማቀላጠፍ በደሴ ፣ በሐዋሳ ፣ በአዳማ እና በሌሎች ቅርንጫፍ ፅ/ቤቶች ላይ አዲሱን የፓስፖርት ስረአት ለማስጀመር እቅድ መያዙ የተገለፀ ሲሆን ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በመስራት የተሻለ ለውጥ ለማምጣት የስራ አፈጻጸም ግምገማ አስፈላጊ መሆኑ ተገልጿል ።
በ2018 የበጀት አመት የጥቅምት ወር ዕቅድ አፈጻጸም ላይ ምክትል ዋና ዳይሬክተሮችን ጨምሮ ፣ የአገልግሎቱ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል ።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
