ጥር 17 ቀን 2018: አዲስ አበባ
የኢሚግሬሽን ሰራተኞች ሸማች ህ/ስ/ማህበር 2ኛ ዓመት 4ኛ መደበኛ ጉባኤውን በደማቅ ሁኔታ አክብሯል። የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት ማህበሩ ከተመሰረተ አጭር ጊዜ ቢሆንም የሰራተኞችን ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ አቅም ከመደገፍ ባለፈ አገልግሎቱ እያከናወናቸው ያሉትን የለውጥ ስራዎችን እየደገፈ መሆኑን ተናግረዋል።
ማህበሩን ከማቋቋም አንስቶ አሁን እስካለበት ደረጃ ለማድረስ ትልቅ ስራ መሰራቱን ያነሱት ክብርት ዋና ዳይሬክተር አሁን ያለበት ደረጃ ለሌሎች ተምሳሌት መሆኑንም ገልጸዋል።በተቋሙ የተከናወኑት የለውጥ ስራዎች አገር አቀፍና አለም አቀፍ ዕውቅና ማግኘቱን የተናገሩት ዋና ዳይሬክተሯ ይህም የአመራሩ እና የሰራተኛው የጋራ ውጤት መሆኑን ገልጸዋል።
ማህበሩን ለማጠናከር ዘርፈ ብዙ ስራዎች መሰራታቸውን ያነሱት ዋና ዳይሬክተሯ በዚህም ለአገልግሎቱ ሰራተኞች የመኖሪያ ቤት ግንባታ የሚውል መሬት በማህበሩ በኩል ከአዲስ አበባ መስተዳደር መሰጠቱን ገልፀው ለተደረገው ትብብር ከተማ መስተዳድሩን አመስግነው ለአገልግሎቱን ሰራተኞች የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
የልደታ ክፍለ ከተማ ህብረት ስራ ማህበር ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ባዬ በሀይሉ በክፍለ ከተማው በርካታ ሸማች ማህበራት መኖራቸውን ገልፀው የኢሚግሬሽን ሰራተኞች የህብረት ስራ ማህበር በተመሰረተ ሁለት አመት ውስጥ ያስመዘገባቸው ስኬቶች በአልግሎቱ ለተከናወኑ ሁሉን አቀፍ ለውጦች ማሳያ መሆኑን ገልጸው ለሌሎች ተቋማት ተምሳሌት መሆኑን ተናግረዋል።
በሸማች ማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ የ2017 በጀት ዓመት የኦዲት እና የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦአል፣የመተዳደሪያ እና ውስጠ ደንብ ማሻሻያ ቀርቦ ፀድቆአል፣በቤት ግንባታ ማደራጃ ማህበር ግንዛቤ ተፈጥሯል በተጨማሪም የ2018 ዕቅድና 6 ወር አፈፃፀም ሪፖርት የቀረበ ሲሆን ሁለት ዓመት የሞላው የማህበሩ የቦርድ እና ቁጥጥር ቴክኒክ ኮሚቴ አመራሮች በአዲስ አመራሮች ተተክተዋል።
በመጨረሻም ማህበሩን ለዚህ ስኬት ላበቁት ለተቋሙ ከፍተኛ አመራሮችና ለማህበሩ ሀላፊዎች ሽልማትና የእውቅና ሰርተፍኬት ተበርክቶአል።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
ሁሉም የሚታወቅባት ኢትዮጵያ !
————————
ለበለጠ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ድረ -ገፆችን ይጎብኙ ይወዳጁን
Telegram: https://t.me/ICS_Ethiopia
Facebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopia
Twitter: https://twitter.com/ics_ethiopia
TikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopia
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopia
YouTube: https://www.youtube.com/@Ics_Ethiopia
Instagram: https://www.instagram.com/icsethiopia/
