አዲስ አበባ ፡ጥር 19/05/2018 ዓ.ም
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በብሄራዊ ደህንነት ዩንቨርሲቲ በዲፕሎማሲና አለማቀፍ ግንኙነት፣ በመረጃ ደህንነት፣በደንበኞች አገልግሎት፣ በስደት ህጎች እና ሌሎች የስልጠና ርእሶች ዙሪያ ለ201 የተቋሙ ሰራተኞች ስልጠና መስጠት ጀምሯል።
በስልጠናው ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ም/ዋና ዳይሬክተርና የዜግነት ዘርፍ ሃላፊ አቶ ቢቂላ መዝገቡ ተቋሙ የአገልግሎት አሰጣጥን ለማዘመን እና የተገልጋዩን ህብረተሰብ እርካታ እውን ለማድረግ የሚያስችል ሰዉ ተኮር ሪፎርም ማከናወኑን አስታዉሰዉ የሰው ኃይል ማሟላት፣ ማልማት እና አቅም መገንባት አንዱ የሪፎርሙ የትኩረት አቅጣጫ መሆኑንም ተናግረዋል።
ተቋሙ ያካሄደዉን ሪፎርም ተከትሎም በእወቀትም በክህሎትም ብቁ የሆኑ አዲስ ሰራተኞችን በመቅጠር የሰው ኃይል ቁጥር ከማሳደግ ባለፈ ተከታታይነት ያለዉ ትምህርትና ስልጠና በመስጠት የአመራርና ሰራተኛዉን አቅም በማሳደግ ላይ ይገኛል ብለዋል። የዚህ ስልጠና ዋና አላማም የሰራተኛውን እና አመራር አቅም በማሳደግ ዜጎችን በቅንነት ፣ በታማኝነት እና በትህትና ለማገልገል የተዘጋጀ የሰዉ ሃይል ማፍራት መሆኑን ተናግረዋል።
አቶ ቢቂላ አያይዘዉም ሰራተኞች ከስልጠናዉ የሚያገኙትን አቅም ወደ ተግባር በመቀየር እንዲሁም በትኩረትና በንቃት በመስራት ደንበኞች በአገልግሎት የሚደሰቱበትና የሚረኩበት ተቋም ለማድረግ በተያዘዉ ሪፎርም የማስቀጠልና የማጽናት ጉዞ ላይ የበኩላቸዉን አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ ጥሪ አቅርበዋል።
በብሄራዊ ደህንነት ዩንቨርስቲ የሚሰጠዉ ይህ ስልጠና በዲፕሎማሲና በአለማቀፍ ግኑኝነት፣ በመረጃ ደህንነት፣ ሽብርተኝነትን በመዋጋት፣ በደንበኞች አገልግሎት፣ በተቋማዊ መዋቅርና ሪፎርም፣ በስደት ህጎች፣ በኢሚግሬሽን ህጎች እና ቱሪዝም፣ በስነምግባርና ጸረ_ሙስና ፣ ጊዜ አጠቃቀም ጨምሮ በሌሎች ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነዉ።
ስልጠናዉ ለቀጣዮቹ ሁለት ሳምንታት እንደሚሰጥ በስልጠናዉ መክፈቻዉ ላይ ተገልጿል።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
ሁሉም የሚታወቅባት ኢትዮጵያ !
————————
ለበለጠ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ድረ -ገፆችን ይጎብኙይወዳጁን
Telegram: https://t.me/ICS_Ethiopia
Facebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopia
Twitter: https://twitter.com/ics_ethiopia
TikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopia
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopia
YouTube: https://www.youtube.com/@Ics_Ethiopia
Instagram: https://www.instagram.com/icsethiopia/
