ለፓስፖርት አገልግሎት ተጠቃሚዎች

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አዲስ ፓስፖርት ለማውጣት የምትፈልጉ ደንበኞቻችን የመደበኛ እና የአስቸኳይ ፓስፓርት አገልግሎት ክፍያ ዋጋ ዝርዝር የሚከተለው ሲሆን አገልግሎቱን ለማግኘት በኦንላይን www.ethiopianpassportservices.gov.et እና www.immigration.gov.et መሙላት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን። ማሳሰቢያ፡- – ክፍያውን በተቋሙ አካውንት ብቻ በማስገባት እና ሌሎች ተጨማሪ ክፍያዎችን ባለመክፈል ራስዎን ከህገ ወጥ ደላሎች ይጠብቁ!!! የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
ለአስቸኳይ ፓስፖርት ፈላጊዎች • Announcement for Urgent Passport Applicants

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ከዚህ በፊት ሲጠቀምበት ከነበረው የኦን ላይን አፕሊኬሽን በተጨማሪ አዲሱን የኢ ፓስፖርት የኦን ላይን አፕሊኬሽን በመጠቀም ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን:- በአዲሱ ሲስተም የምንሰጠው አገልግሎት ማሳሰቢያ:- ወደተቋማችን ሲመጡ የፋይዳ መታወቂያ እና ኦን ላይን ያመለከታችሁበትን ፕሪንት አውት ይዛችሁ እንድትመጡ እናሳስባለን። የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት The Immigration and Citizenship Service is pleased to announce that in addition […]
የአምስተኛ ዙር ጥሪ

በኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት መጋቢት 14 ቀን 2017 ዓ.ም የተሠጠውን ፈተና ወስዳችሁ የቃለመጠይቅ ፈተና የተፈተናችሁ አመልካቾች በአገልግሎት ተቋሙ የውድድር መስፈርት መሠረት ለስራ ቅጥር ያለፋችሁ ስም ዝርዝራችሁን ከዚህ በታች የለቀቅን ሲሆን ሰኔ 06/2017 ዓ.ም 2:30 ሰዓት ጎተራ በሚገኘው ቢሯችን ሪፖርት እንድታደርጉ እየገለጽን ከተጠቀሰው ቀን ውጪ የሚመጡ አመልካቾችን የማናስተናግድ መሆኑን እናሳውቃለን። ጥብቅ ማሳሰቢያ:- ማንነታችሁን የሚገልፅ መታወቂያ፣ 4 ጉርድ […]
የቃል ፈተና ጥሪ

በኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ከሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች መጋቢት 14/2017 ዓ. ም የተሠጠውን የፅሁፍ ፈተና ለወሠዳችሁ አመልካቾች በሙሉ፡- ከ50 በላይ የአመጣችሁ የፈተና ውጤት ከዚህ በታች የገለፅን ስለሆነ እንድትመለከቱ እያሳሰብን ጎተራ በሚገኘው ቢሯችን ሰኔ 3/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:30 በመገኘት የቃል ፈተና እንድትወስዱ እናሳውቃለን። ማሳሰቢያ:- ማንነታችሁን የሚገልፅ መታወቂያ እና 2 ጉርድ ፎቶ ይዛችሁ መምጣት ይጠበቅባችኋል። የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
የአራተኛ ዙር ጥሪ

በኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት መጋቢት 13 ቀን 2017 ዓ.ም የተሠጠውን ፈተና ወስዳችሁ የቃለመጠይቅ ፈተና የተፈተናችሁ አመልካቾች በአገልግሎት ተቋሙ የውድድር መስፈርት መሠረት ተጠባባቂ ሁናችሁ ለስራ ቅጥር ያለፋችሁ ከዚህ በታች ስም ዝርዝራችሁን የለቀቅን ሲሆን ግንቦት 25/2017 ዓ.ም 2:30 ሰዓት ጎተራ በሚገኘው ቢሯችን ሪፖርት እንድታደርጉ እየገለጽን ከተጠቀሰው ቀን ውጪ የሚመጡ አመልካቾችን የማናስተናግድ መሆኑን እናሳውቃለን። ጥብቅ ማሳሰቢያ:- ማንነታችሁን የሚገልፅ መታወቂያ፣ […]
የዳግም ምዝገባ ጥሪ ስለማድረግ • Immigration Service Calls for In-Person Re-registration of Companies Inviting Foreign Nationals

ለስራም ይሁን ለአጫጭር ስብሰባዎች የውጭን ሀገር ዜጋ ለምትጋብዙ ተቋማት/ኩባንያዎች በሙሉ:- አገልግሎት መስሪያ ቤቱ አዲስ ባስጀመረው የተቋማት መመዝገቢያ ሲስተም ላይ ተቋማችሁን/ኩባንያዎቻችሁን ከ ግንቦት 15 /2017 ዓ.ም ጀምሮ አስፈላጊ ሰነዶችን በመያዝ ጎተራ በሚገኘው የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና መስሪያ ቤት በአካል በመቅረብ እንድታስመዘግቡ እናሳስባለን። ካምፓኒያችሁን ለማስመዝገብ የሚመጣ ማንኛውም ጉዳይ አስፈፃሚ እራሱም ጉዳይ አስፈፃሚ ሆኖ እንዲመዘገብ ከድርጅቱ የተጻፈለትን ደብዳቤ […]
ፋይዳ እንዴት ልመዝገብ?
ለአዲስ አበባ አስቸኳይ ፓስፖርት አመልካቾች በሙሉ

ከዚህ ቀደም አዲስ የአስቸኳይ ፓስፖርት በኦን ላይን ለመሙላት እንደተቸገራችሁ በተደጋጋሚ ማሳወቃችሁ ይታወሳል። ስለሆነም በኦን ላይን ብቻ ስንሰጥ የነበረውን የአዲስ አስቸኳይ ፓስፖርት አገልግሎት የክቡራን ደንበኞቻችን ፍላጎት ከግምት በማስገባት አማራጭ መንገድ የተከተልን በመሆኑ ተገልጋዮች ከግንቦት 04/09/2017 ዓ.ም ጀምሮ አስፈላጊ ሰነዶችን በመያዝ ጥቁር አንበሳ በሚገኘው የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት መ/ቤት በአካል በመምጣት መስተናገድ የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እናሳውቃለን። ማሳሰቢያ:- […]
ውጤት ስለማሳወቅ

በኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ከሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጣችሁ እና ከመጋቢት 26 እስከ ሚያዚያ 2 ቀን 2017 ዓ/ም የተሠጠውን የቃል ፈተና ለወሠዳችሁ አመልካቾች በሙሉ፡- በፅሁፍ እና በቃል ፈተና ውጤት ያለፋችሁ እንዲሁም በተጠባባቂነት የተያዛችሁ አመልካቾች ከታች ተያይዞ የቀረበውን ዝርዝር መረጃ እንድትመለከቱ እያሳሰብን የአገልግሎት ተቋሙ የቅጥር ሂደቱን እና የስልጠና ፕሮግራምን በተከታታይ በተቋሙ ድህረ ገፅ እና በሁሉም ማህበራዊ ሚዲያዎች […]
የሁለተኛ ዙር ጥሪ

በኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት መጋቢት 13 ቀን 2017 ዓ.ም የተሠጠውን ፈተና ወስዳችሁ የቃለመጠይቅ ፈተና የተፈተናችሁ አመልካቾች በአገልግሎት ተቋሙ የውድድር መስፈርት መሠረት ለስራ ቅጥር ያለፋችሁ ከዚህ በታች ስም ዝርዝራችሁን የለቀቅን ሲሆን ሚያዚያ 27ቀን 2017 ዓ.ም 7:00 ሰዓት ጥቁር አንበሳ በሚገኘው ቢሯችን ሪፖርት እንድታደርጉ እየገለጽን ከተጠቀሰው ቀን ውጪ የሚመጡ አመልካቾችን የማናስተናግድ መሆኑን እናሳውቃለን። ማሳሰቢያ:- 4 ጉርድ ፎቶ እና […]
