በኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ከሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች መጋቢት 14/2017 ዓ. ም የተሠጠውን የፅሁፍ ፈተና ለወሠዳችሁ አመልካቾች በሙሉ፡-
ከ50 በላይ የአመጣችሁ የፈተና ውጤት ከዚህ በታች የገለፅን ስለሆነ እንድትመለከቱ እያሳሰብን ጎተራ በሚገኘው ቢሯችን ሰኔ 3/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:30 በመገኘት የቃል ፈተና እንድትወስዱ እናሳውቃለን።
ማሳሰቢያ:-
ማንነታችሁን የሚገልፅ መታወቂያ እና 2 ጉርድ ፎቶ ይዛችሁ መምጣት ይጠበቅባችኋል።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
