በኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት መጋቢት 14 ቀን 2017 ዓ.ም የተሠጠውን ፈተና ወስዳችሁ የቃለመጠይቅ ፈተና የተፈተናችሁ አመልካቾች በአገልግሎት ተቋሙ የውድድር መስፈርት መሠረት ለስራ ቅጥር ያለፋችሁ ስም ዝርዝራችሁን ከዚህ በታች የለቀቅን ሲሆን ሰኔ 06/2017 ዓ.ም 2:30 ሰዓት ጎተራ በሚገኘው ቢሯችን ሪፖርት እንድታደርጉ እየገለጽን ከተጠቀሰው ቀን ውጪ የሚመጡ አመልካቾችን የማናስተናግድ መሆኑን እናሳውቃለን።
ጥብቅ ማሳሰቢያ:-
ማንነታችሁን የሚገልፅ መታወቂያ፣ 4 ጉርድ ፎቶ፣ ከ8ኛ ክፍል ጀምሮ ያለውን የትምህርት ማስረጃ ዋናውን እና 1 ኮፒ ይዛችሁ መምጣት ይጠበቅባችኋል።
ለ1 ሳምንት የስልጠና ማዕከል የምትገቡ ስለሆነ አስፈላጊውን ዝግጅት በማድረግ በተጠቀሰው ቀን እንድትገኙ እያሳሰብን ስልጠናው እንደተጠናቀቀ ቀጥታ ወደ ሰራ የምትገቡ ይሆናል።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
