ለፓስፓርት አገልግሎት አመልካቾች በሙሉ! • Important Notice for Passport Service Applicants

በአስቸኳይ ወይም በመደበኛ አግልግሎት ፓስፓርት ለማውጣት አመልክታችሁ በ7876 አሻራ እና ፎቶ እንድትሰጡ አጭር የፅሁፍ መልዕክት የደረሳችሁ ደንበኞቻችን የቀጠሮ ቀናችሁ ከመድረሱ በፊት ኦሪጅናል ሰነዶችን (ኦርጅናል የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ፥ የተረጋገጠ የልደት የምስክር ወረቀት እና ፋይዳ መታወቂያ) ይዞ ወደ ቢሮአችን በመምጣት መስተናገድ የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን ።

ማሳሰቢያ፡ ቀጠሮ ቀናችሁ ካለፈ በኋላ የሚመጡ ከሆነ ግን  የማናስተናግድ መሆኑን እናሳስባለን።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት

Important Notice for Passport Service Applicants

For those who have applied for an urgent or regular passport service and have received an SMS from 7876 instructing you to provide fingerprints and photos:
Please be informed that before the date of your appointment, you must come to our office with the original documents — your renewed kebele ID, certified birth certificate, and fayda (digital) ID — to be able to receive service.

Reminder:
If you come after the date of your appointment has passed, we will not be able to serve you.

Immigration and Citizenship Service