በኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት መጋቢት 13 ቀን 2017 ዓ.ም የተሠጠውን ፈተና ወስዳችሁ የቃለመጠይቅ ፈተና የተፈተናችሁ አመልካቾች በአገልግሎት ተቋሙ የውድድር መስፈርት መሠረት ለስራ ቅጥር ያለፋችሁ ከዚህ በታች ስም ዝርዝራችሁን የለቀቅን ሲሆን ሚያዚያ 27ቀን 2017 ዓ.ም 7:00 ሰዓት ጥቁር አንበሳ በሚገኘው ቢሯችን ሪፖርት እንድታደርጉ እየገለጽን ከተጠቀሰው ቀን ውጪ የሚመጡ አመልካቾችን የማናስተናግድ መሆኑን እናሳውቃለን።
ማሳሰቢያ:-
4 ጉርድ ፎቶ እና ከ8ኛ ክፍል ጀምሮ ያለውን የትምህርት ማስረጃ ዋናውን እና 1 ኮፒ ይዛችሁ እንድትመጡ እናሳስባለን።
