ከዚህ ቀደም አዲስ የአስቸኳይ ፓስፖርት በኦን ላይን ለመሙላት እንደተቸገራችሁ በተደጋጋሚ ማሳወቃችሁ ይታወሳል።
ስለሆነም በኦን ላይን ብቻ ስንሰጥ የነበረውን የአዲስ አስቸኳይ ፓስፖርት አገልግሎት የክቡራን ደንበኞቻችን ፍላጎት ከግምት በማስገባት አማራጭ መንገድ የተከተልን በመሆኑ ተገልጋዮች ከግንቦት 04/09/2017 ዓ.ም ጀምሮ አስፈላጊ ሰነዶችን በመያዝ ጥቁር አንበሳ በሚገኘው የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት መ/ቤት በአካል በመምጣት መስተናገድ የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እናሳውቃለን።
ማሳሰቢያ:- የቅ/ፅ/ቤቶች አይመለከትም።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
