በሕዝብ  ተወካዮች  ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች  ቋሚ ኮሚቴ የሲቪልና የቤተሰብ ምዝገባ ስርዓት ረቂቅ አዋጁ መሻሻል በኢትዮጵያ ዘመናዊ የሕዝብ  አስተዳደር ለማስፈን ፋይዳው የጎላ መሆኑን ገልጿል።

ቋሚ ኮሚቴው ይህን ያለው በሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ ስርዓት ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ  ላይ ከአስረጂዎች እና ከባለድርሻ አካላት  ጋር በተወያዩበት ወቅት ነው።

በማሻሻያ ረቂቅ አዋጁ የወሳኝ ኩነቶችን መረጃዎች በዘመናዊ ቴክኖሎጂ መዝግቦ መያዝ የህዝቡን ጥቅም ለማረጋገጥ እና የተጀመረውን ልማት ከግብ ለማድረስ ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳለው ቋሚ ኮሚቴው አመላክቷል።

የውጭ ግንኙነት እና የሰላም  ጉዳዮች  ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ዲማ ነጎ (ዶ/ር) የረቂቅ አዋጁ መሻሻል ዘረፈ- ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው ገልጸው ረቂቅ አዋጁን የበለጠ  ለማደበርና ግብዓት ለመሰብሰብ ተጨማሪ መድረኮች እንደሚካሄዱ ነው ያስገነዘቡት።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት በበኩላቸው የረቂቅ አዋጁ መሻሻል ዋና መርህ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን ተጠቅሞ የወሳኝ ኩነት መረጃዎችን ምዝገባ ማካሄድ ነው ያሉ ሲሆን አክለውም  የዘርፉን የመረጃ አያያዝ ማዘመን የተሻለ የሕዝብ ተጠቃሚነት እንዲኖር እና ልማቱን ለማፈጠን የላቀ ጠቀሚታ አንዳለው ገልጸዋል።

በኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የህግ አገልገሎት ዳይሬክተር ወ/ሮ ወንጌል ይግለጡ  የረቂቅ  አዋጁ መሻሻል የወሳኝ ኩነት መረጃዎችን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመያዝ የመንግሥት ፖሊሲና ስትራቴጂዎችን በአግባቡ ለመተግበር፤ መልካም አስተዳደር ስርዓትን ማስፈን እና ወንጀልን ለመከላከል እንደሚያስችል አብራርተዋል።

በረቂቅ  አዋጁ ልደት በ90፣ ሞት በ50 ቀናት ሎሎች ኩነቶች ደግሞ በ30 ቀናት ውስጥ መመዝገብ እንዳለባቸው የተካተተ መሆኑን የገለጹት ወ/ሮ ወንጌል፤ እነዚህን መረጃዎች በተቀመጠው ጊዜ ገደብ ያላስመዘገበ ከ5 መቶ እስከ 5 ሺህ ብር ቅጣት መደንገጉን ተናግረዋል።

በማሻሻያ ረቂቅ አዋጁ በተለያዩ አንቀጾች ትርጉምን ጨምሮ መሻሻልና መካተት አለባቸው ያሏቸውን ቁልፍ ጉዳዮች የውይይት መድረኩ ተሳታፊዎች ጠቁመዋል።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት