የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ከኦሮሚያ፣ አማራ፣ አፋር፣ ቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልሎችና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለተውጣጡ ወንድ 159 ሴት 69 ድምር 228 የክብር መዝገብ ሹሞችና አስተባባሪዎች በሲቪል ምዝገባ መሰረታዊ ጉዳዮች እና በመረጃ ምንነት፣ጥራትና አጠባበቅ ላይ የመጀመሪያ ዙር ስልጠና ሰጠ።









ስልጠናው በአዳማ፣ በጎንደር፣ በኮምቦልቻና በአሶሳ የተሰጠ ሲሆን የስልጠናው ዋና ዓላማም ከሲቪል ምዝገባ የሚገኘው መረጃ ጥራት ያለው እንዲሆንና ለሚፈለገው አላማ እንዲውል የሚያስችል ግንዛቤ ለመፈጠር እና የክብር መዝገብ ሹሞች በምዝገባ ሂደት የሚፈጥሯቸው የአመዘጋገብ ክፍተቶችን በማሳየት በተቻለ ፍጥነት የሚስተካከሉበትን ሁኔታ ለማመቻቸት እንደሆነ ተገልፆል፡፡
በአገር አቀፍ ደረጃ በማንዋል እየተካሄደ የሚገኘው የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ወደ ዘመናዊ ቴክኖሎጅ ምዝገባ ስርዓት በመሸጋገር ላይ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን አሁን ላይ ያለው ምዝገባ እንደ አገር ጥቅም ላይ ሊውሉ የሚችሉ ጥራት ያላቸው መረጃዎችን ከማመንጨት አንጻር ውስንነት እንዳለው በመገንዘብ በሁሉም መዝጋቢ ተቋማት የዲጂታል ምዝገባ ስርዓት በፍጥነት መጀመር እንዳለበት ተነግሯል።
ስልጠናው በ2ኛ ዙር በተለያዮ ክልሎችና ከተማ አስተዳደር የሚሰጥ ሲሆን በቀጣይ የሚሰጠውን የወሳኝ ኩነት አገልግሎት ቀልጣፋና ጥራት ያለው እንዲሆን እንደሚያግዝ ተጠቁሟል።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
