የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ከሁሉም ክልሎችና የከተማ መስተዳድር የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ኤጀንሲ የእቅድ ዝግጀትና ሪፖርት ዳይሬክተሮችና ባለሙያዎች ለተወጣጡ ሰልጣኞች ግንቦት 25/2016 ዓ.ም በአዳማ ከተማ ስልጠና ሰጥቷል።
በስልጠናው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ የስትራቴጂክ ዕቅድ ዝ/ድ/ቁ/ግ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ጌታቸው በአገር አቀፍ የሚተገበረው የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ስርአት ደረጃውና ጥራቱ የጠበቀ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ለመተግበር በወሳኝ ኩነት መዝጋቢ አካላት ተቀናጅቶ መስራት አስፈላጊ መሆኑ ገልፀዋል። አክለውም እንደ ሀገር ጥራት ያለው የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ለማጠናከር በሁሉም መዝጋቢ አካላት ላይ ተቀራራቢ ግንዛቤ በመፍጠር ደረጃው የጠበቀ የእቅድና የሪፖርት ስርዓት መከተል አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል።



በመጨረሻም ስልጠናው በወሳኝኩነት መዝጋቢ አካላት የሚስተዋሉ ክፍተቶች በማረም የምዝገባ ሽፋንና ጥራት ለማጠናከር የሚያስችል መሆኑን ተገልጿል። የእቅድና ዝግጅት አተገባበር የስልጠና ሰነድ በአቶ ዘሩባቤል ትርሲት፣ እንዲሁም የድጋፍ፣ ክትትልና ግምገማ ስርዓት የስልጠና ሰነድ በአቶ ግርማ ባሻ ቀርበው በስልጠናው ተሳታፊዎች ውይይት ተደርጎባቸዋል።
