በአዲስ አበባ ከተማ አዲስ የሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ ሲስተም ተጀመረ

አዲስ አበባ፡ ህዳር 26/2018 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በይፋ የተጀመረዉ አዲሱ ሲስተም የሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት አሰጣጥን ይበልጥ የሚያዘምን እንዲሁም አዲስ የተቀናጀ የሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት ሥርዓትን ለመዘርጋት የሚያግዝ መሆኑን ከንቲባዋ ገልጸዋል።

በኢሚግሬሽን፣ በጤና፣ በፍርድ ቤት፣ በብሔራዊ መታወቂያ እና በሎሎችም ተቋማት መካከል ቅንጅት እና መናበብን የሚፈጥር እንደሆነ ከንቲባ አዳነች ጠቁመዋል።

ሥራ ላይ የዋለው የ”Civil Registration and Vital Statistics with ID” ሲስተም ባለጉዳዮች የሞባይል ስልካቸውን፣ የተለያዩ የቴክኖሎጂ አማራጮችን በመጠቀም በአካል ሳይገኙ ባሉበት ሆነው አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችል ነው ተብሏል።

አዲሱን ሲስተም ያበልጸገዉ የኢትዮዽያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲቲዩት ሲሆን ሲስተሙን በማበልጸግ ሂደት ወቅት የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ከፍተኛ እገዛ ማድረጉን የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ወርቁ ጋቸና ገልጸዋል።በቀጣይም ከአዲስ አበባ በተጨማሪ በቀጣይ በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች ይህን ሲስተም የመዘርጋት ስራ እንደሚሰራ ተናግረዋል።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት ይህ በአዲስ አበባ የተጀመረዉ ሲስተም ፍርድ ቤቶች እና ጤና ተቋማት ከአገልግሎቱ ጋር ያላቸዉን ትብብር የሚያጠናክር እና በአንድ አይነት ሲስተም እንዲጠቀሙ በማስቻል የልደት፥ ሞት እና ሌሎች ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባን ተናባቢ እና ወጥነት ያለው እንዲሆን ተቋሙ የያዘዉን እቅድ እዉን ለማድረግ ትልቅ እገዛ ይኖረዋል ብለዋል።

ሲስተሙ የሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎትን ወደ ኦንላይን በማሻገር ሀገሪቱን የሚመጥን ዘመናዊ፣ ጥራቱን እና ደረጃውን የጠበቀ የምዝገባ ሥርዓትን ለመዘርጋት ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረዉም ወይዘሮ ሰላማዊት ገልጸዋል።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ ስርአቱን የመመዝገብ፥ የመምራት፥ የማስተባበር እና የመደገፍ ተልኮዉን ለመወጣት እንዲችል የምዝገባ ስርዓቱን ዲጂታላይዝ በማድረግ አሰራሩን ለማዘመን እንደተቋም የአምስት ዓመት ስትራቴጅክ እቅድ አውጥቶ እየሰራ መሆኑ ይታወቃል።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት

ሁሉም የሚታወቅባት ኢትዮጵያ !

————————

ለበለጠ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ድህር -ገፆችን ይጎብኙ ይወዳጁን …….

Telegram: https://t.me/ICS_EthiopiaFacebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopiaTwitter: https://twitter.com/ics_ethiopiaTikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopiaLinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopiaYouTube: https://www.youtube.com/@Ics_EthiopiaInstagram: https://www.instagram.com/icsethiopia/

Latest Posts

Any Questions?

Call us!

8133