በኢትዮጵያ የሚኖሩ እና ሕጋዊ የመኖሪያ ሰነድ የሌላቸው የውጭ ሀገር ዜጎች ሰነዳቸውን ሕጋዊ እንዲያደርጉ የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ጥሪ አቀረበ።
የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት ጉዳዩን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ
• ሐሰተኛ ሰነድ ያላቸው የውጭ ሀገር ዜጎች እና የኢሚግሬሽን ስርአትን ሳያሟሉ በህገ ወጥ መንገድ ወደ ሀገር ገብተው እየኖሩ ያሉ እና ህጋዊ ስርዓት ውስጥ ያልገቡ፣
• ቪዛ እና የመኖሪያ ፈቃድ ሳያድሱ በህገ ወጥ መንገድ ከተፈቀደላቸው ጊዜ በላይ የሚቆዩ እና
• ካምፓኒ ምዝገባ ሳያከናውኑ የውጭ ዜጐችን እያሰሩ ያሉ ተቋማቶች መኖራቸውን በተደረገ ማጣራት አረጋግጠናል ብለዋል።
እነዚህ ሕጋዊ ሰነድ የሌላቸው ዜጎች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑን ያነሡት ዋና ዳይሬክተሯ ከጥር 1 እስከ ጥር 30 ቀን 2016 ዓ.ም በ1 ወር ጊዜ ውስጥ ወደ ተቋሙ ዋና መ/ቤት በመቅረብ እንዲመዘገቡ እና ወደ ህጋዊ የምዝገባ ስርአት እንድትገቡ ጥሪ አቅርበዋል።



