ቅርንጫፍ ፅ/ቤቱ በሰሜን ኢትዮጲያ በተከሰተው ግጭት ምክንያት ከጥቅምት 2013 ዓ.ም ጀምሮ ተዘግቶ መቆየቱ ይታወቃል። ከሰኔ 11፣ 2016 ዓ.ም ዳግም አገልግሎት የጀመረ ሲሆን፣ በጊዜያዊነት የጀመራቸው አገልግሎቶች ፓስፓርት ማደስ፣ የጠፋ ፓስፖርት መተካት እና የተበላሸ ወይ እርማት የመስጠት ናቸው።



በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ፓስፖርታቸው ሲያሳድሱ አግኝተን ያነጋገርናቸው የመቐለ ከተማ ነዋሪዎች የቅርንጫፉ አገልግሎት በመቋረጡ ምክንያት አዲስ አበባ ድረስ ለመሄድ ይገደዱ እንደነበሩና በዚሁም በርካታ አላስፈላጊ እንግልት ይደርስባቸው እንደነበር ጠቅሰው ዳግም ስራ በመጀመሩ መደሰታቸውን ገልጸዋል።
