ከሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ልዑካን ጋር ውይይት ተደረገ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 10 ፣ 2018 ዓ.ም በሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ፀሃፊ ቀሲስ ታጋይ ታደለ የሚመራው የልዑካን ቡድን የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በለውጥ ሂደት አዲስ የስራ ምዕራፍ የመጡ ለውጦች የሚደነቁ ለሌሎችም ተቋማት በተምሳሌትነት የሚነሱ መሆናቸውን በውይይቱ ላይ አንስተዋል።

የአገልግሎቱን የስራ እንቅስቃሴ እና የመጣውን ለውጥ በተመለከተ በአገልግሎቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተሮች በክቡር ኢንጅነር ጎሳ ደምሴ እና በክቡር አቶ ቢቂላ መዝገቡ ሰፊ ገለፃ የተደረገላቸው ልዑካኑ በሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ ዙሪያ በጋራ መስራት እንደሚገባም አንስተዋል።

የሃይማኖት ተቋማት ዋና ፀሃፊ ቀሲስ ታጋይ ታደለ በተቋሙ በኩል አስፈላጊው ድጋፍ ሁሉ እንደሚደረግ ቃል ገብተዋል።

የልዑካን ቡድኑ በተቋሙ የመጣው ለውጥ የሚታይ መሆኑን ጠቅሰው የአሰራር ሂደትን ከማሻሻል ባሻገር በህግ የተደገፈ የመዋቅር ህዳሴ የታየበት መሆኑን በማንሳት በጋራ እንደሚሰሩ ገልፀዋል።

በተጨማሪም የተለያዩ ሀይማኖታዊ ጉዞዎች በሚኖሩበት ጊዜ አገልግሎቱ ላደረጋቸው ትብብሮች የሀይማኖት ጉባኤው አመስግኖአል።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት

ሁሉም የሚታወቅባት ኢትዮጵያ !

————————

ለበለጠ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ድህረ -ገፆችንን ይጎብኙ ይወዳጁን ……

Telegram: https://t.me/ICS_EthiopiaFacebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopiaTwitter: https://twitter.com/ics_ethiopiaTikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopiaLinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopiaYouTube: https://www.youtube.com/@Ics_EthiopiaInstagram: https://www.instagram.com/icsethiopia/