ከ800ሺህ በላይ ደንበኞች በቅርንጫፍ ብቻ ለአዲሱ ኢ-ፓስፖርት አመልክተዋል

ከ800ሺህ በላይ ደንበኞች በቅርንጫፍ ብቻ ለአዲሱ ኢ-ፓስፖርት አመልክተዋል – ሰላማዊት ዳዊት የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር

አዲስ አበባ ፣ ጥር 6 ፣ 2018 ዓ.ም የአፈፃፀም አቅምን በማጎልበት የአገልግሎት አድማስን በጥራት እና በፍጥነት ለማዳረስ በየ ዘርፉ የተሰሩ ስራዎች ከነባሩ ስረአት ወደ አዲሱ አሰራር ያለ እንከን ለመሸጋገር አቅም የፈጠሩ መሆኑን የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት የተቋሙ የ2018 በጀት ዓመት የስድስት ወር ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በቀረበበት ወቅት አንስተዋል ።

የኢ-ፓስፖርት አገልግሎት በሁሉም  ቅርንጫፎች መሰጠት በመጀመሩ ከ800ሺህ በላይ ደንበኞች በቅርንጫፍ ብቻ ለአዲሱ ኢ-ፓስፖርት ማመልከታቸውየ2018 በጀት ዓመት የስድስት ወር ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ግምገማ ላይ ተገልጿል ።

የአገልግሎት ፈላጊዎችን እርካታ የተሻለ ለማድረግ እስካሁን ከተሰራው በበለጠ ወደ ፊት በተሟላ የአገልግሎት ጥራት እና ተደራሽነት እንደሚሰራ ዋና ዳይሬክተሯ ገልፀው እቅድን መሰረት ባደረገ መልኩ የተናበበ ስራ መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል ።

በተቋሙ የተሰሩ የሪፎርም ስራዎችን በማፅናት በቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት አሻራ የመቀበል እና አዲሱን ኢ-ፓስፖርት መጀመሩን በማንሳት እስካሁንም ከ800ሺህ በላይ ደንበኞች በቅርንጫፍ ብቻ ለአዲሱ ፓስፖርት ማመልከታቸውን ገልፀዋል ።

በተለያየ የህግ-ወጥ መንገድ የተሰማሩ 99 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን፤ 83 የዉጭ ዜጎች ተጠያቂ በማድረግ 11 ቤቶች ታሽገዋል ፣ሰነድ በማጭበርበር 6,395 የዉጭ ዜጎች እና 3,126 ኢትዮጵያውያን ላይም እርምጃ መወሰዱ ለነጻ እና ህጋዊ የሰዎች ዝውውር መደላድል መፈጠሩን የገለፁት ዋና ዳይሬክተሯ በስድስት ወር አፈጻጸም ነጻ የሰዎችን እንቅስቃሴ በማመቻቸት እና በማሻሻል ለ3,795,043 ተጓዞች አገልግሎት ተሰቷል ብለዋል ።

የሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ ስርዓትን በማዘመን የምዝገባ ስርዓቱን ከማኑዋል ወደ ዲጂታል ስረአት ለማሸጋገር ባጭር ጊዜ ዉስጥ ትልቅ ተስፋ ሰጪ ሲስተም ማልማት መቻሉ በበጀት ዓመቱ የስድስት ወር ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ላይ ተገልጿል ።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት

ሁሉም የሚታወቅባት ኢትዮጵያ !

————————

ለበለጠ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ድረ -ገፆችን ይጎብኙይወዳጁን

Telegram: https://t.me/ICS_EthiopiaFacebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopiaTwitter: https://twitter.com/ics_ethiopiaTikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopiaLinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopiaYouTube: https://www.youtube.com/@Ics_EthiopiaInstagram: https://www.instagram.com/icsethiopia/