የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ከኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት  ኃላፊዎች ጋር በቅንጅት በሚሰሩ ስራዎች ዙሪያ ተወያዩ።

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ከኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት እና ም/ዋና ዳይሬክተሮች ጋር ውይይት አካሂደዋል።

ውይይቱ ከውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት አኳያ ሁለቱ ተቋማት የሚሰጡትን አገልግሎት ፈጣንና ቀልጣፋ ለማድረግ ያለመ ነው።

በዚህም በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ላይ የተደረገውን ሪፎርም ተከትሎ በዘረጋው የጋራ የአሰራር ስርዓት የተከናወኑ ሥራዎችን፣ ያጋጠሙ ችግሮችን እና ችግሮቹን ለመሻገር የሚወሰዱ እርምጃዎችን በዝርዝር ተመልክተዋል፡፡ 

ከዚህ ባለፈም የቀጣይ ዓመት ዕቅድ ግልጽና የተቀላጠፈ አሰራር ስርዓትን በማስፈን የተጀመሩትን ዜጎችን በህጋዊ መንገድ  ለስራ ወደ ውጭ የመላክ ስራ በቴክኖሎጂ በታገዘ መልኩ አፈፃፀሙን ከፍ በሚያስችል መልኩ የሚዘጋጅበት ሁኔታ ላይም ውይይት በማካሄድ ስምምነት ላይ መድረስ ተችሏል::