አዲስ አበባ ታህሳስ ፣ 21/2018 ዓ.ም
መንግስት የሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ መረጃዎችን ለዲጂታል የማንነት መታወቂያ ሥርዓት ግንባታ፣ ለፖሊሲ ቀረፃ፣ ለሀገራዊ የልማት ዕቅዶችና የምዕተ ዓመቱን የልማት ግቦችን ለማሳካት የተቀረጹ አመልካቾችን ለመመዘን እና ወሳኝ ግብዓቶች ለሀገራዊ ብልፅግና ለማዋል የሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ በዲጅታል አማካኝነት እየሰራበት መሆኑን የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት በውይይቱ አንስተዋል ።
ዲጂታል የሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ የአስተዳደር፣ የፍትሕ ፣ የሀገር ደህንነትና የመረጃ ሉአላዊነትን በማረጋገጥ ለዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ መሳካት ሚናው ትልቅ ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሯ ፤የሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ የባለድርሻ አካላትን ያካተተ ገቢራዊ እንቅስቃሴ እንደሚፈልግ አስገንዝበዋል ።
አርቴፊሻል ኢንተለጀንስን በመጠቀም አንድ ሰው አንድ የሚሆንበትን ሂደት መፍጠር ላይ የባለድርሻ አካላት ሚና አይተኬ ነው ያሉት የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር እና የዜግነት ዘርፍ ሃላፊ ክቡር አቶ ቢቂላ መዝገቡ የመረጃ ክፍተትን በጋራ ማረም እንደሚገባ አንስተዋል።
በአለም ደረጃ ተስተካካይ የሆነ ስረአት ለመገንባት ሀገራዊ ቁመና ለመመስረት ከባለድርሻ አካላት ጋር ተናቦ መስራት ፤ ሁሉም ሰው የሚታወቅባትን ኢትዮጵያን ለመገንባት እና አንድ የፖለቲካ ማህበረሰብ ለመፍጠር ጭምር የሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ አጋዥ መሆኑን የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር እና የኢሚግሬሽን ዘርፍ ሃላፊ ክቡር አቶ ጎሳ ደምሴ ገልጸዋል ።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በአዋጅ በተሰጠው ስልጣን መሰረት ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት የሲቪል ምዝገባ ውክልና ስቷል ።
በውይይቱ ላይ ከሀገር መከላከያ ሚንስተር ፣ ከጤና ሚንስተር ፣ ሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚንስተር ፣ ከፍትህ ሚንስተር ጨምር ከሌሎች የባለድርሻ ተቋማት የተውጣጡ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል ።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
ሁሉም የሚታወቅባት ኢትዮጵያ !
————————
ለበለጠ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ድህር -ገፆችን ይጎብኙ ይወዳጁን …….
Telegram: https://t.me/ICS_EthiopiaFacebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopiaTwitter: https://twitter.com/ics_ethiopiaTikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopiaLinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopiaYouTube: https://www.youtube.com/@Ics_EthiopiaInstagram: https://www.instagram.com/icsethiopia/
