አዲስ አበባ ፣ የካቲት 30 ፣ 2018 የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት “50 ዓመት የሴቶች ድምፅ ለእኩልነትና ለበለጸገች ኢትዮጵያ ” በሚል መሪ-ሃሳብ የሴቶች ቀንን እያከበረ ይገኛል ዕለቱን በማሰብ የሴቶች የመፈጸም አቅምን ለማሳየት የውጭ ዜጎች አገልግሎት ፣ የውጪ ዜጎች ምዝገባ እና ቁጥጥር እንዲሁም የቪአይፒ የፓስፖርት አገልግሎት በሴቶች ብቻ እየተሰጠ ይገኛል ።
በክብረ በአሉ ላይ የተገኙት የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት የሴቶች ሁለንተናዊ አስተዋጽኦ ለሀገር እድገት መሰረት ለተቋም ግንባታ እርሾ መሆኑን አንስተዋል ።
የሴቶች ሚና በሀገር እድገት በማህበረሰብ ግንባታ የማይተካ ነው በማለት ሴቶች በትጋት በመሆን ካሰቡት መድረስ ይችላሉ ብለዋል።
ተቋሙ ሴቶችን ለማብቃት ዘርፍ ብዙ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል ያሉት የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት ሴቶች የመፈፀም አቅማቸውን ፣ የስራ ትጋታቸውን ለማጎልበት በሁኔታዎች ሳይበገሩ መትጋት እንዳለባቸው ገልፀዋል።
የአገልግሎቱ ስራተኞች በስራ ገበታቸው ላይ ሆነው ያለ ስጋት ይሰሩ ዘንዳ የህፃናት ማቆያ ማዕከል ግንባታ የተመረቀ ሲሆን እናቶች በዚህ ማዕከል ልጆቻቸውን በቅርብ ሆነው መከታተል መቻላቸው የተፈጥሮ ሂደትን በማስቀጠል ላይ ተቋሙ ዝግጁ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሯ ገልፀዋል ።
ዕለቱን ምክንያት በማድረግ ከጤና ሚንስትር ጋር በመተባበር የጡት ካንሰር ምርመራ በነፃ ለተቋሙ ስራተኞችም እየተሰጠ ይገኛል ።
በክብረ በአሉ ላይ የአገልግሎቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተሮችን ጨምሮ የስራ ሃላፊዎች የተቋሙ ሰራተኞች ተገኝተዋል ።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
ሁሉም የሚታወቅባት ኢትዮጵያ !
————————
ለበለጠ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ድህረ -ገፆችንን ይጎብኙ ይወዳጁን ……
Telegram: https://t.me/ICS_Ethiopia
Facebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopia
Twitter: https://twitter.com/ics_ethiopia
TikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopia
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopia
YouTube: https://www.youtube.com/@Ics_Ethiopia
Instagram: https://www.instagram.com/icsethiopia/
