የተቋሙን የእቅድ አፈፃፀም በተለዋዋጭ አለማቀፍ ሁኔታ ውስጥ ማፅናት ይገባል – ክብርት ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 24 ፣2018 ዓ.ም የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የሶስት አመት የገቢ አፈፃፀም በጀትና የቀጣይ ሶስት አመት የገቢ እቅድ ላይ ውይይት አድርጓል፥ ከ2016 -2018 ዓ.ም በጀት ዓመት እቅድ የተሳካ እንደ ነበር የተገለፀ ሲሆን፤ ቀጣዩም ይሳካ ዘንድ በትኩረት መስራት አስፈላጊ መሆኑን የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት በውይይቱ ላይ አንስተዋል።

የስራ ስኬት ለማምጣት እና የአገልግሎት ፈላጊውን እርካታ ከፍ በማድረግ ሀገራዊ ሃላፊነትን ለመወጣት በእቅድ መጓዝ እንደሚገባ ዋና ዳይሬክተሯ አንስተዋል።

በዚ የሶስት አመታት የገቢ አፈፃፀም እና የቀጣይ ሶስት አመታት የገቢ እቅድ ውይይት ላይም እራስን በሁሉም መስክ ለማብቃት እና የተቋሙን ራዕይ ለማሳካት እቅድን መሰረት አድርጎ መስራት ለስኬት አጋዥ መሆኑን ያነሱት የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር  ክብርት ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት ተቋሙን ተለዋዋጭ በሆኑ አለማቀፍ ሁኔታዎች ለማፅናት ሁሉም በእቅድ መጓዙ አስፈላጊ መሆኑን አክለዋል።

በውይይቱ ላይ የተቋሙ ምክትል ዋና ዳይሬክተሮችን ጨምሮ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች እና ሰራተኞች በመገኘት ገንቢ ሃሳብ ስተዋል።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
ሁሉም የሚታወቅባት ኢትዮጵያ !
————————
ለበለጠ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ድህረ -ገፆችንን ይጎብኙ ይወዳጁን ……
Telegram: https://t.me/ICS_Ethiopia
Facebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopia
Twitter: https://twitter.com/ics_ethiopia
TikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopia
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopia
YouTube: https://www.youtube.com/@Ics_Ethiopia
Instagram: https://www.instagram.com/icsethiopia/