የአለማቀፉ ስደተኞች ድርጅት ከኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ጋራ ትብብሩ እንደሚቀጥል አስታወቀ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 25፣ 2018 ዓ.ም

የድንበር አስተዳደር እና ቁጥጥር የሰው ሀብት ልማት ፤ የልምድ ልውውጥ የቴክኖሎጂ ሽግግር ፤ ወደ ኢትዮጵያ የሚደረጉ ህገወጥ ስደቶች እና ፍልሰቶችን መቆጣጠር የሚያስችል የጋራ ስረአት መዘርጋት ላይ ውይይቱ የተደረገ ሲሆን በትብብር እና በቴክኖሎጂ አማካኝነት ወጥነት ያለው የድንበር ቁጥጥር ስረአትን መተግበር ለህጋዊ የሰዎች እንቅስቃሴ አስፈላጊነቱ በምክክሩ ላይ ተነስቷል ።

ከአለማቀፉ የስደተኞች ድርጅት እና ከሲዊዘርላንድ መንግስት ጋራ በመሆን በድንበር ቁጥጥር ዙሪያ ጥራቱን የጠበቀ መረጃ ለመሰብሰብ፣ለማከማቸት፣ ለተጠቃሚ ምቹ የሆነ፣ ጠቃሚ የድንበር አስተዳደር መረጃ ሥርዓትን ከማንዋል ወደ ዲጅታል በመላው የድንበር አውታር የመረጃ መረብ ውስጥ የተጓዥ መረጃን ለማደራጀት እንደሚሰራ በውይይቱ ላይ የተገለፀ ሲሆን የጉዞ እና የፍልሰት ሂደትን ለመቆጣጠር ማይዳስ (MIDAS) የተሰኘ መርሃግብር  የዜጎችን የሀገር ሀገር ጉዞ ህጋዊነት ከፍ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የገለፁት የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት ቴክኖሎጂን የሚጠቀም ፣ የቁጥጥር ባለሞያዎችን ለማብቃት በጋራ እንደሚሰራ ገልፀዋል ።

በትብብር በመተግበር ላይ የሚገኘው ማይዳስ (MIDAS) የህጋዊ መረጃ ቁጥጥር ስረአት ህገወጥ ጉዞ እና ስደትን ከመቆጣጠር ባለፈ የሀገራትን ሰላም እና ደህንነት ማስጠበቅ ላይ የራሱን የሆነ መሰረት በመጣል የመረጃ ቁጥጥር ሂደትን ዲጂታላይዝ በማድረግ ውስጥ የማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ጉዞን የሚያፋጥን ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሯ መርሃግብሩ በአገልግሎቱ የጀመርነው የሪፎርም ስራ በከፍተኛ ደረጃ የሚያግዝ ነው ብለዋል ።

በኢትዮጵያ የስዊዘርላንድ አምባሳደር ሪካርዳ ቻንዳ በኢትዮጵያ የተሻሻለ የሰው ልጅ ደህንነት የጉዞ ሂደት እና የድንበር ደህንነት፣ መተግበሩ ለዜጎች ደህንነት ወሳኝ መሆኑን አንስተው፤
በቀጣይ ኢትዮጵያ ፈጣን አቅርቦት እንድታገኝ በማድረግ፣ ይበልጥ ቀልጣፋ፣ ደህንነቱን የተጠበቀ የኢሚግሬሽን አገልግሎቶች ለመስጠት በትብብር መንግስታቸው ከአገልግሎቱ ጋራ እንደሚሰራ ገልፀዋል ።

የአለማቀፉ ስደተኞች ድርጅት በኢትዮጵያ ተወካይ አቢባቱ ዋኔ ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂ አማካኝነት ዘመናዊ እና ጠንካራ የድንበር አስተዳደር በመተግበር ከማኑዋል ቁጥጥር ወደ ዲጂታል ስረአት ለመቀየር እና ስደተኞችን ለመቀበል ያላት ቁርጠኝነት የሚደነቅ መሆኑን ገልጿል ።

ይህ የድንበር ቁጥጥር ፕሮጀክት በስዊዘርላንድ የገንዘብ ድጋፍ በአውሮፓ ህብረት የተሻለ የፍልሰት አስተዳደር እና በጀርመን ፌዴራላዊ የኢኮኖሚ ትብብር እና ልማት ሚኒስቴር በኢትዮጵያ ይተገበራል ።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
ሁሉም የሚታወቅባት ኢትዮጵያ !
————————
ለበለጠ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ድህር -ገፆችን ይጎብኙ ይወዳጁን …….
Telegram: https://t.me/ICS_Ethiopia
Facebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopia
Twitter: https://twitter.com/ics_ethiopia
TikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopia
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopia
YouTube: https://www.youtube.com/@Ics_Ethiopia
Instagram: https://www.instagram.com/icsethiopia/

Latest Posts

Any Questions?

Call us!

8133