የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልገሎት ሁለተኛውን ዋና መስሪያ ቤት በጅማ ከተማ ሊገነባ ነው

ታህሳስ፡ ጅማ/17/ 2018 ዓ.ም

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በሰው ተኮር የሪፎርም ስራዎቹ የለውጥ መስኮችን በመለየት ጥልቅ ተቋማዊ የሪፎርም ስራዎችን በመስራት ላይ የሚገኝ መሆኑ የሚታወቅ ነው ያሉት የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር እና የዜግነት ዘርፍ ሃላፊ የሆኑት ክቡር አቶ ቢቂላ መዝገቡ ይህ የጅማው ሁለተኛው ዋና መስሪያ  ቤት ሌላ የለውጥ ምዕራፍ ይሆናል ብለዋል ።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ሁለተኛውን የዋና መስሪያ ቤት ግንባታ በጅማ ከተማ ለመገንባት የሚያስችለው ሂደት ላይ ከከተማው አመራሮች ጋራ ውይይት ያደረገ ሲሆን ለተሟላ አገልግሎት ለማህበረሰቡ ፍላጎት ግንባታው አስፈላጊ መሆኑን የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር እና የዜግነት ዘርፍ ሃላፊ የሆኑት ክቡር አቶ ቢቂላ መዝገቡ ገልፀዋል ።

በነበረው ውይይት ላይ የቦታ ርክክብ ፣ የግንባታ ፍቃድ የዲዛይን ስራዎች ፣ የስራ ሂደትን በመፍጠር እና መፍጠን መርህ በአጭር ግዜ ውስጥ ለመከወን የሚያስችል ገንቢ ውይይት ከከተማው ባለድርሻ አካላት ውይይት ተደርጓል ።

በጅማ ከተማ የሚገነባው የዋና መስሪያ ቤት ግንባታ የሰው ተኮር ሪፎርማችን ማሳያም ነው ያሉት የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር እና የዜግነት ዘርፍ ሃላፊ የሆኑት ክቡር አቶ ቢቂላ መዝገቡ በተሻለ ጥራት ዋና መስሪያ ቤቱ ይገነባል ብለዋል ።

በመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መንግስት ወደ ማህበረሰቡ በመቅረብ ችግሮችን ከመሰረቱ በመቅረፍ ትልቅ ለውጥ ማምጣት የሚቻልበትን የአሰራር ስረአት ዘርግቷል ያሉት ክቡር  አቶ ቢቂላ መዝገቡ።

እኚህ ስራዎች የተሳለጠ የድንበር እንቅስቃሴ ለመፍጠር ፣ ዜጎች የታወቀ ማንነት እንዲኖራቸው እና የብሄራዊ መረጃ ደህንነትን ለማረጋገጥ አጋዥ መሆናቸውን አንስተው የአንድ ማዕከል አገልግሎቶች የዲጂታል ኢትዮጵያን 2030 ከማሳካት ባለፈ ዜጎች የሚፈልጉትን አገልግሎት በአንድ ማዕከል በእኩልነት ከማግኘት በተጨማሪ በተቋሙ ላይ የበለጠ እምነት እንዲኖራቸው የሚያስችል መሆኑን አስገንዝበዋል ።

ተቋሙ በዚህ መንገድ በአራቱም የሀገሪቱ ማዕዘናት የተሟላ ግልጋሎት እየሰጠ እንደሚገኘ ምክትል ዳይሬክተሩ አስታውሰው በቀጣይም በሐዋሳ ፣ በድሬዳዋ ፣ ባህርዳር ከተሞች ላይ ሁለተኛ ዋና መስሪያ ቤት እንደሚገነባ አንስተዋል።

Tajaajilli Immigreeshiniifi Lammummaa Itoophiyaa hojiilee haaromsa tajaajila si’ataa dhugoomsan hedduu hojii irra oolcha jira.

Hojiilee haaromsaa keessa tokko giddugala tajaajila fooddaa tokko ykn Masoobii yoo ta’u, hojii tajaajila fooddaa tokko gara tokkootti fiduuf guddigalli tajaajila kanneeni iddoo gara garaatti ijaaruf xiyyeeffannaan hojjetamaa jira.

Daariktarri Olaanaa itti Aanaafi itti gaafatamaan dhimma lammummaa Obbo Biqilaa Mazgabuu Magaalaa Jimmaatti haala ijaarsa waajjira olaanaa lammaaffaa irratti qaamoolee dhimmi ilaallattu waliin mari’achuun walharkaa fuudhinsa Diizayiniifi iddoo ijaarsaa gochuun hojiin ijaarsaa akka eegalamu ibsaniiru.

Hojiileen riifoormii Tajaajilli immigreeshiniifi lammummaa gaggeessaa jiru haalan lafa qabachuun bu’aa olaanaa galmeessaa jiraachuu kan himan Obbo Biqilaan, imalaa fi to’onnaa daangaa jabeessuu, lammiileen eenyuma beekame akka qabataniifi dantaa biyyaa eegsisuu keessatti shoora olaana qabaachuu ibsaniiru.

Dabalataan karoora Itoophiyaa dijitaalaa 2030 milkeessuufi lammiileen tajaajila walfakkaataafi si’ataa iddoo tokkotti akka argatanuifi amantii dhaabbaticha irraa qaban daran kan cimsu ta’uu himan. Hojiileen ijaarsaa kunneenis, Bahaar Daar, Dirree Dhawaafi Hawaasatti yeroo dhiyootti akka eegalaman eeraniiru.

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት

ሁሉም የሚታወቅባት ኢትዮጵያ !

————————

ለበለጠ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ድህር -ገፆችን ይጎብኙ ይወዳጁን …….

Telegram: https://t.me/ICS_EthiopiaFacebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopiaTwitter: https://twitter.com/ics_ethiopiaTikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopiaLinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopiaYouTube: https://www.youtube.com/@Ics_EthiopiaInstagram: https://www.instagram.com/icsethiopia/