አዲስ አበባ ፡ ታህሳስ 25/04/2018 ዓ.ም
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በብሄራዊ ደህንነት ዩንቨርሲቲ በመረጃ ደህንነት፣በደንበኞች አገልግሎት፣ በዲፕሎማሲና አለማቀፍ ግኑኝነት፣ በስደት ህጎች እና ሌሎች የስልጠና ርእሶች ዙርያ ለ148 የተቋሙ ሰራተኞች ሲሰጥ የነበረዉን ስልጠና አጠናቋል።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተርና የኢሚግሬሽን ዘርፍ ሃላፊ አቶ ጎሳ ደምሴ ተቋሙ ባለፉት ሁለት አመታት 11 የሪፎርም አጀንዳወችን በመንደፍ የአገልግሎት አሰጣጥን ለማዘመን እና የተገልጋዩን ህብረተሰብ እርካታ እውን ለማድረግ የሚያስችል ሰዉ ተኮር ሪፎርም ማድረጉን አስታዉሰዉ በአሁኑ ወቅትም ይህን ሪፎርም የማስቀጠልና የማፅናት ስራ እየተከናወነ ነዉ ብለዋል።
ከ11 የሪፎርም አጀንዳወች መካከል የሰው ኃይል ማሟላት፣ ማልማት እና አቅም መገንባት አንዱ የሪፎርሙ የትኩረት አቅጣጫ መሆኑን ያስታወሱት አቶ ጎሳ ይህ በተለያዩ ተቋማት እየተሰጠ ያለዉ ስልጠናም በእዉቀት እና በክህሎት የበቃ፣ የነቃ እንዲሁም አቅም ያለዉ አገልጋይ በመፍጠር ተቋሙ የተሰጠዉን የአገልግሎት እና የቁጥጥር ሃላፊነት መወጣት የሚችል ሰራተኛ ማፍራት መሆኑን ተናግረዋል።
የአገልጋይነት መንፈስ የተላበሰ ሰራተኛ እና አመራር መፍጠር ይህን ተከትሎም የተገልጋዩን ህብረተሰብ እርካታ እና የነገዉን ትዉልድ ታሳቢ ያደረገ በቴክኖሎጅ የታገዘ የአሰራር ስርአት መዘርጋት ተቋሙ ትኩረት ሰጥቶት እየሰራ መሆኑን ያውሱት አቶ ጎሳ ሰልጣኞች በስልጠናዉ ያገኙትን እዉቀትና ክህሎት ወደ ተግባር በመቀየር ሪፎርሙን በማስቀጠል እና በማጽናት ተቋማዊ ብሎም ሃገራዊ ሃላፊነታቸዉን ሊወጡ እንደሚገባም አሳስበዋል።
ም/ዋና ዳይሬክተሩ አክለዉም ተቋሙ ከአገልጋይነት በተጨማሪ የሀገር ደህንነት መቆጣጠርና መጠበቅ ሃላፊነት የተሰጠዉ መሆኑን ገልጸዉ ሰልጣኞች በሚሰሩበት ቦታ የዜጎችን መብት እንዲሁም የሀገሪቱን ብሄራዊ ጥቅም እና ብሄራዊ ደህንነት በጠበቀ መልኩ በታማኝነት እና በቅንነት ከእኔ አይቅር በሚል ስሜት በመስራት የተሻለ አገልጋይ ሊሆኑ እንደሚገባም ጥሪ አቅርበዋል።
በብሄራዊ ደህንነት ዩንቨርስቲ ለሁለት ሳምንት ሲሰጥ የቆየዉ ይህ ስልጠና በዲፕሎማሲና በአለማቀፍ ግኑኝነት፣ በመረጃ ደህንነት፣ ሽብርተኝነትን በመዋጋት፣ በደንበኞች አገልግሎት፣ በተቋማዊ መዋቅርና ሪፎርም፣ በስደት ህጎች፣ በኢሚግሬሽን ህጎች እና ቱሪዝም፣ በስነምግባርና ጸረ_ሙስና ፣ ጊዜ አጠቃቀም ጨምሮ በሌሎች ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነበር።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
ሁሉም የሚታወቅባት ኢትዮጵያ !
————————
ለበለጠ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ድረ -ገፆችን ይጎብኙይወዳጁን
Telegram: https://t.me/ICS_Ethiopia
Facebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopia
Twitter: https://twitter.com/ics_ethiopia
TikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopia
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopia
YouTube: https://www.youtube.com/@Ics_Ethiopia
Instagram: https://www.instagram.com/icsethiopia/
