ከኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት፣ የጤና ሚኒስቴር፣ ከኢትዮዽያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት እንዲሁም ከክልልና ከተማ መስተዳድሮች የተወጣጡ አመራርና ባለሙያዎች በአዳማ ከተማ ከግንቦት 22 እስከ 23/2016 ዓ/ም ለሁለት ቀናት የቆየ የዘጠኝ ወራት ቅንጅታዊ አሰራርና የአፈፃፀም ግምገማ ማድረጉን ገልፀዋል።
በክብር እንግድነት ተገኝተው የግምገማ መድረኩን የከፈቱት በኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ፅሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ወልዴ፤ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በአገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረው የሲቪል ምዝገባ ለማጠናከርና ለማዘመን ከባለድርሻና አጋር አካላት በቅንጅት መስራት ወሳኝ መሆኑን ገልፀዋል። የሲቪል ምዝገባ ለፍትሕና አስተዳደር ከሚሰጠው አገልግሎት በተጨማሪ ለስታቲስቲክስ አገልግሎት የሚውል ጥራት ያለው መረጃ ለመሰብሰና ለማደርጀት የሚያስችል የዲጂታል ምዝገባ ስርአት በፓይለት ደረጃ በሁሉም ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች መጀመሩን ገልፀዋል።






አክለውም የተጀመረው ቅንጅታዊ ስራን አጠናክሮ በማስቀጠል በአምስት አመታት ስትራቴጂክ እቅድ ላይ የተቀመጡ ግቦችን ለማሳካት ባለድርሻና አጋር አካላት የበኩላቸውን እንዲወጡ አሳስበቧል።
በግምገማ መድረኩ የተለያዩ ጥናቶችና የአፈፃፀም ሪፖርቶች ቀርበው ሰፊ ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን የነበሩ ጠንካራና ደካማ ጎኖች እንዲሁም ያጋጠሙ ችግሮችን በመለየት በቀጣይ ጠንካራ ቅንጅታዊ አሰራር በመፍጠር የተሻለ አፈፃፀም ለማምጣት አቅጣጫ ተቀምጠዋል።
