የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት ተቋሙ ባለፉት 30 ቀናት ውስጥ ሲሰራቸው የነበሩ ስራዎች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በዚህም ለተገልጋዮች ቅሬታ ” የፓስፖርት ህትመት ዕጥረት ዋና ችግር ” መሆኑን ገልፀው ችግሩን ለመፍታት 190 ሺህ ፓስፖርት በአንድ ወር ውስጥ ወደ ሀገር ቤት መግባቱን አስታውቀዋል።
ፓስፖርት ለመውሰድ ከተመዘገቡ ከስድስት ወር በላይ ለሆናቸው ዜጎች ፓስፖርት የመስጠት ስራ እንደሚሰራም ተገልጿል፡፡
የፓስፖርት ቀጠሮ ያለፈባቸው ደንበኞች ዘወትር ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡30 – 6፡3ዐ ሰአት ድረስ በመምጣት መስተናገድ የሚችሉ መሆኑን አሳውቀዋል።
ከሙስናና ብልሹ አሰራር ጋር በተያያዘም በርካታ ደላሎች እና ህገ ወጥ አሰራር ላይ የተሳተፉ አካላት በህግ ቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን ገልፀው ከተቋሙ ውጭ የሆኑ ደላሎች የሀሰት ማስረጃዎችን፣ ፓስፖርቶችን የተቋሙ በማስመሰል እና ሀሰተኛ ዌብሳይቶችን በማዘጋጀት ህብረተሰቡን ለህገወጥ ድርጊት እየዳረጉ በመሆኑ ህ/ሠቡ ይህንን አውቆ ጥንቃቄ እንዲያደርግና ትክክለኛ የተቋሙን ዌብሳይት በመለየት መጠቀም እንዳለበት አሳውቀዋል፡፡





