የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት ተቋሙ ባለፉት 100 ቀናት ውስጥ ሲሰራቸው የነበሩ ስራዎች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በዚህም ለተገልጋዮች ቅሬታ ” የፓስፖርት ህትመት ዕጥረት ዋና ችግር ” መሆኑን ገልፀው ችግሩን ለመፍታት 531,800 ፓስፖርት ወደ ሀገር ቤት መግባቱን አስታውቀዋል።
በዚህ መሰረት በሀገር ውስጥ፡-
አዲስ አበባ 45,366 ፓስፖርት ታትሞ ለስርጭት አጭር የፅሁፍ መልዕክት የተላከ ሲሆን
ከዚህ ውስጥ ፓስፖርት የወሰደ ተገልጋይ 29, 442 (64.9%) ሲሆን የፅሁፍ መልዕክት ደርሷቸው ፓስፖርታቸውን ያልወሰዱ 15, 924
(35%) መሆኑን እና ቀላል የማይባል ተገልጋይ ፓስፖርት ታትሞለት እንዲወስድ ጥሪ የቀረበ ቢሆንም እስካሁን ቀርቦ ያልወሰደ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
አስቸኳይ ጉዳይ ኖሯቸው በአስቸኳይአገልግሎት የተስተናገዱ 15,793 ሲሆን የክልል ተገልጋዮችን ህትመት በመጀመር 8500 ፓስፖርት ታትሞ ለክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች በዛሬው እለት እየተላከ መሆኑን ገልፀው
በአጠቃላይ በአገር ዉስጥ ለ69,659 ተገልጋዮች ፓስፖርት በማሳተም የማሰራጨት ስራ መሰራቱን አሳውቀዋል።
በውጭ አገር ለሚኖሩ ዜጎች
እስካሁን ለተለያዩ ሀገራት በDHL በኩል 33, 083፣ በኦንላይን ላመለከቱ 7,448
በአጠቃላይ በዉጭ ለሚኖሩ 40,531 ዜጎች አገልግሎት መስጠት ተችሏል፡፡
በሙስና እናበብልሹ አሰራር የተጠረጠሩ
በእስር ላይ በፍርድ ሂደት ላይ የሚገኙ የተቋሙ ሰራተኞች አጠቃላይ 38 (34 ወንድ እና 4 ሴቶች) እና ከእነዚህ ግለሰቦች ጋር በውጭ በኔትወርክ ተሳስረው የሚሰሩ 15 ደላሎችን በድምሩ 53 ግለሰቦች በህግ ጉዳያቸው እየታየ መሆኑን አሳውቀው ማህበረሰቡና የሚዲያ አካላት አሁንም ብልሹ አሰራርን ለመከላከል እንዲተባበር ጥሪ አስተላልፈው አንዳንድ ህገወጦች ሀሰተኛ ዌብሳይቶችን በማዘጋጀት ህብረተሰቡን ለህገወጥ ድርጊት እየዳረጉ በመሆኑ ህ/ሠቡ ይህንን አውቆ ጥንቃቄ እንዲያደርግና ትክክለኛ የተቋሙን ዌብሳይት በመለየት መጠቀም እንዳለበት አሳውቀዋል፡፡




