የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት የቻይና ብሔራዊ የኢምግሪሽን አስተዳደር ምክትል ኃላፊ ኮሚሽነር ሊዩ ሃይታኦ በቢሮአቸው ተቀብለው አነጋገሩ።

የሁለቱ ተቋማት ከፍተኛ ኃላፊዎች በቅንጅት አብሮ መስራት በሚያስችላቸው ጉዳዮች በተለይም የኢሚግሬሽን ዘርፉን ከማዘመን፣ የድንበር ቁጥጥር ስርዓቶችን ማሻሻል እንዲሁም የአቅም ግንባታ ዙሪያ የመከሩ ሲሆን በተለይ ሕጋዊ  የጉዞ ሰነዶችን ከሐሰተኛ ሰነዶች (forged documents) መለየት በሚያስችሉ ቴክኖሎጂዎች ዙሪያ ልምድ ለመለዋወጥ እና ድጋፍ ለማድረግ ተስማምተዋል፡፡ 

የቻይና ብሔራዊ የኢምግሬሽን አስተዳደር ምክትል ኃላፊ ኮሚሽነር ሊዩ ሃይታኦ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎትን ለልምድ ልውውጥ ወደ ተቋማቸው ጋብዘዋል።

ክቡር ምክትል ኮሚሽነር ሊዩ ሃይታኦ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ልዩ ሚና የምትጫወት ሀገር መሆኗን አንስተው ዘርፉን ማዘመንና ማሻሻል በዓለም አቀፍ የህዝብ ደህንነት ዙሪያ ከፍተኛ ሚና የሚጫወት መሆኑን ተናግረዋል።