የክቡር ዶክተር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ከክብርት ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት ጋራ ተወያዩ

አዲስ አበባ መጋቢት ፣ 16 ፣ 2018 ዓ.ም የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ፕሬዚዳንት የሆኑትን የክቡር ዶክተር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋን በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው በጋራ በሚሰሩባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።

የክቡር ዶክተር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ አገልግሎቱ በሐጅ እና ዑምራ ጉዞ ለህዝበ ሙስሊሙ ለሰጠው ልዩ አገልግሎት እና ድጋፍ አመስግነው በቀጣይም በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በጋራ እንደሚሰሩ አስገንዝበዋል።

አክለውም የክቡር ዶክተር ሸይኽ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ በተቋሙ የመጣው ለውጥ የአሰራር ሂደት መሻሻልን አድንቀዋል።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
ሁሉም የሚታወቅባት ኢትዮጵያ !
————————
ለበለጠ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ድህረ -ገፆችንን ይጎብኙ ይወዳጁን ……
Telegram: https://t.me/ICS_Ethiopia
Facebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopia
Twitter: https://twitter.com/ics_ethiopia
TikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopia
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopia
YouTube: https://www.youtube.com/@Ics_Ethiopia
Instagram: https://www.instagram.com/icsethiopia/