በኢምግሬሽንና የዜግነት አገልግሎት ስር ነቀል ለውጥ ተደርጓል የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬ አለት በሰጡት ማብራሪያ ላይ የኢምግሬሽንና የዜግነት አገልግሎት በአጭር ግዜ ውስጥ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣቱን ተናግረዋል።

አገልግሎቱ የተሟላ ሪፎርም ማድረጉን ጠቅሰው ተቋሙ ኢትዮጵያን የሚመጥን ታሪኩን ማዕከል ያደረገ ለውጥ ላይ መሆኑን ገልፀዋል ።

ባለፉት ሶስት አመታት በተሰራ የሪፎርም ስራ የኢትዮጵያ የፓስፖርት አቅም ከ270ሺ ወደ 4 ሚልዮን ከፍ ማለቱን የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬ አለት የኢምግሬሽንና የዜግነት አገልግሎት ባጠረ ግዜ ውስጥ ያመጣውን ለውጥ በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ ላይ አንስተዋል ።የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
——
Telegram: https://t.me/ICS_Ethiopia
Facebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopia
Twitter: https://twitter.com/ics_ethiopia
TikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopia
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopia
YouTube: https://www.youtube.com/@Ics_Ethiopia
Instagram: https://www.instagram.com/icsethiopia/