በ2018 በጀት ዓመት የአገልግሎቱ ትኩረት የተገልጋይ እርካታን ማረጋገጥ እንደሆነ ተገለፀ። 

አዲስ አበባ: 29/09/2017 ዓ.ም

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ማናጅመንት  በ2018 በጀት ዓመት መሪ ዕቅድ ቀጣይ አቅጣጫ ላይ ውይይት  አድርጓል። 

በውይይቱ ወቅት የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት ባለፉት ጊዜያት አገልግሎቱ ተደራሽነት ላይ ትኩረት ተደርጎ ሲሰራ እንደነበር ገልፀው በቀጣይ ዓመት የላቀ የተገልጋይ እርካታ ላይ እንደሚሰራ   ተናግረዋል። 

አክለውም የሪፎርም ስራዎችን የማስቀጠልና የማፅናት ስራ እንደሚሰራ እና ከቁልፍ ባለድርሻ አካላት ጋር የሚኖረው ግንኙነት በሰፊው እንደሚሰራበት ገልፀዋል።

በውይይቱ የ2018 በጀት አመት ከተለመደው መንገድ በመውጣት መሰረታዊ ለውጥ የሚመጣበት ዓመት መሆን እንዳለበት ተመላክቷል።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት

——