አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2017
ለ20ኛው የዓለም የሥራ ድርጅት አህጉራዊ ጉባኤ መሳካት አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት የእውቅና ስነ-ስርዓት በትላንትናው ምሽት በኢንተር-ሌግዤሪ ሆቴል ተካሂዷል፡፡
በዚህም ኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ከ2000 በላይ እንግዶች እና 30 ሚኒስትሮችን የቪዛ እና የኢሚግሬሽን አገልግሎት በተቀላጠፈ መንገድ በመስጠት አህጉራዊ ጉባኤው በስኬት እንዲጠናቀቅ ላበረከተው አስተዋፅኦ የእውቅና ሽልማት ተበርክቶለታል፡፡
