ሐምሌ 16/2017 ዓ.ም
ኢትዮጵያና ኔዘርላንድስ በኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ዘርፍ ያላቸውን ትብብር የበለጠ ለማጠናከር ተስማምተዋል።
በኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት የተመራ እና ከተለያዩ ተቋማት የተውጣጣ የስራ ሀላፊዎችን ያካተተ የልዕካን ቡድን በኔዘርላንድስ የስራ ጉብኝት እያካሄደ ያለ ሲሆን፣ልዑካን ቡድኑም የስደተኞችና ስደት ተመላሾች አገልግሎት ም/ዋና ዳይሬክተር፣በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአውሮፓና አሜሪካ አገራት ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ጄነራልእንዲሁም በቤልጂየም የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ምክትል ሚሲዮን መሪን ጨምሮ ሌሎችንም አካላት ያካተተ ነው።
ጉብኝቱ በዋናነት በሁለቱ አገራት ፀንቶ የቆየውን ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነትና ትብብር ከማጠናከር ባሻገር ኔዘርላንድስ በኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዘርፍ፣ በድንበር እና በማቆያ ማዕከላት አስተዳደር እንዲሁም ከስደተኞችና ተመላሾች ዘርፍ ያሉ መልካም ተሞክሮዎችን ለመቅስም ያለመ ነው። ልዑኩ ከዚህ ጋር በተያያዘ በአገሪቱ የተለያዩ ተቋማትን እየተዟዟረ በመጎብኘት ዘርፉን ከሚመሩ የተለያዩ የስራ ሃላፊዎች ጋር ትብብርን ማጠናከር የሚያስችሉ ጠቃሚ ውይይት ማካሄድ ችሏል። የኔዘርላንድስ የኢሚግሬሽን ተቋም ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ቡድን ባለፈው የካቲት ወር ላይ በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት ማድረጋቸው የሚታወስ ነው።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
