የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ጎሳ ደምሴ የቱርክ መንግስት የፍልሰት አስተዳደር የሉዑካን ቡድንን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው ያነጋገሩ ሲሆን በአገልግሎት መ/ቤቱ የፍልሰት ፓሊሲዎች፣ የአሰራር ማዕቀፎች እና የድንበር ተሻጋሪ እንቅስቃሴዎችን ለመቆጣጠር የሚያስችል አሰራር መኖሩን ገልፀው አሁን ላይ እያጋጠሙ ያሉ ተግዳሮቶችን በዝርዝር አስረድተዋል::





በውይይቱ የሁለትዮሽ የትብብር ጥረቶችን ለማጎልበት፣ ከስደት ተመላሾች ጋር እና ሌሎች ተያያዥ ስራዎችን መሰረት ያደረጉ ስራዎችን ለመስራት ፣ ተቋማዊ ግንኙነቶችን ለማጠናከር እና በትብብር ለመስራት መስማማታቸው ተገልፆል።
