የኢትዮጵያ አዲሱ ኢፓስፓርት የሬድ ዶት ብራንድ እና ኮሙዩኒኬን ዲዛይን ሽልማት አሸናፊ ሆነ

አዲስ አበባ: 29/02/2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ አዲሱ የኢ-ፓስፖርት  በዲዛይኑ ባካተተው የደህንነትና ሌሎችም ይዘቶች በአለምአቀፍ ደረጃ የ2025 የሬድ ዶት ብራንድስ  እና ኮሚንኬሽንስ ዲዛይን ተሸላሚ ሆነ።
የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር  ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት በጀርመን በርሊን በተካሄደው የሽልማት ስነስርዓት ላይ በመገኘት ሽልማቱን ተቀብለዋል።

ከወራቶች በፊት ይፋ የተደረገዉ ይህ አዲሱ የኢትዮጵያ ኢ-ፓስፖርት ጥብቅ የደህንነት ባህርያትን በመያዝ ፣ ለየት ባለ ዲዛይኑ እና አስደናቂ ታሪካዊ ይዘቶችን ማካተቱ የአለምአቀፉ የሬድ ዶት ዲዛይንና ኮሙኒኬሽን ሽልማት አሸናፊ እንዲሆን አስችሎታል ።

ፓስፓርቱ የግለሰቦችን ባዮሜትሪክና ባዮግራፊክ መረጃዎች ሰንዶ ከመያዝ ባሻገር ዋልያ አይቤክስ፥ ሉሲ ድንቅነሽ፥ የአክሱም ሀውልት ፥ የግእዝ ቁጥር ፥አደይ አበባን ጨምሮ ሌሎች የኢትዮጵያ መለያ የሆኑ ታሪካዊ ፥ባህላዊና  ተፈጥሯዊ መስህቦችን በውስጡ የያዘ መሆኑም ለሽልማት እንዲበቃ ማስቻሉም ነዉ የተገለጸዉ።
ፓስፓርቱ ምስጢራዊነት እና ደህንነትን በዲዛይኑ ውስጥ አካቶ መያዙም ሌለው ለሽልማት እንዲበቃ ያስቻለው ጉዳይ መሆኑና  ይህም  ሽልማት በኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት እየተከናወነ ላለው ሪፎርም ማሳያ መሆኑን የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት ገልፀዋል።

ይህ እዉቅና በተቋሙ  የተጀመርነውን ስር ነቀል ለውጥ ይበልጥ ከፍ ለማድረግ እንዲሁም የተቀላጠፈ ስራ በቀጣይ ይበልጥ ለመስራት የሚያበረታታ መሆኑንም ወይዘሮ ሰላማዊት ገልጸዋል።

የሬድ ዶት ብራንድ እና ኮሙዩኒኬሽን ሽልማት በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ዝና ያለው ሲሆን ለምርቶች እና ለኢንዱስትሪ ዲዛይን ፣ ለብራንድ እና ለግንኙነት ዲዛይን እንዲሁም ለዲዛይን ፅንሰ-ሀሳቦች  እውቅና የሚሰጥ ዓመታዊ  የዲዛይን እና ፈጠራ ሽልማት መሆኑ ይታወቃል።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት

——

Telegram: https://t.me/ICS_Ethiopia
Facebook: https://www.facebook.com/ICSEthiopia
Twitter: https://twitter.com/ics_ethiopia
TikTok: https://www.tiktok.com/@ics_ethiopia
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/icsethiopia
YouTube: https://www.youtube.com/@Ics_Ethiopia
Instagram: https://www.instagram.com/icsethiopia/
https://www.red-dot.org/de/project/the-new-ethiopian-epassport-84459