የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ አዋጅ ላይ ከተለያዮ አጋር እና ባለድርሻ አካላት ቴክኒካል ቡድን ጋር ተወያየ።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ ስርአት የሚስተዋሉበትን ክፍተቶች ለመሙላት ነባሩን አዋጅ እንዲሻሻል ማድረጉ ይታወሳል።

በዚህም በጸደቀው የሲቪል እና ቤተሰብ ምዝገባ አዋጅ ማሻሻያ፣ የአዋጅ ማስፈጸሚያ ረቂቅ ደንብ፣ የምዝገባ ማስፈጸሚያ መመሪያዎች ላይ የጋራ መግባባት ለመፍጠር ከተቋሙ ባለድርሻ እና ተባባሪ አካላት ቴክኒካል ቡድን ጋር በአርባ ምንጭ ከተማ ለሁለት ቀናት የቆየ የምክክር መድረክ እንደተደረገ ተገልፆል።

ነገም የፌደራል እንዲሁም የሁሉም የክልልና ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ ኃላፊዎች በተገኙበት የምክክር መድረኩ እንደሚቀጥል ተነግሯል።