የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ወቅታዊ እና ጥራቱን የጠበቀ የሲቪል ምዝገባ እና ቤተሰብ ምዝገባ ስርአት ለመዘርጋት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ገለፀ። 

ጅማ፡ ጥቅምት 3 ቀን 2018 ዓ.ም

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ለ8ኛ ጊዜ የተከበረውን የሲቪል ምዝገባ እና ቫይታል ስታቲስቲክስ ቀን አስመልክቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር የፓናል ውይይት አካሂዷል። 

 በኢትዮጵያ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ  አጠቃላይ ሂደት እና እድገት ላይ እንዲሁም የልደት፥ ጋብቻ፥ ፍቺ፥ ጉዲፈቻ፥ ሞት እና ሌሎች የሲቪል ምዝገባ እና ቤተሰብ ምዝገባ ደንብ እና በብሄራዊ ዲጅታል መታወቂያ ዙሪያ  ጽሁፎች ቀርበው የፓናል ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

የፓናል ውይይቱ ተሳታፊዎች የሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ አሰራሮችን ሙሉ ለሙሉ ዲጅታላይዝ ማድረግ፥ ከትምህርት እና ምርምር ተቋማት ጋር በቅንጅት በመስራት፥ የአመራርና የህብረተሰቡን ግንዛቤ ማሳደግ፥ ከከተሞች በተጨማሪ በገጠርና ድንበር አካባቢ የምዝገባ ሽፋኑን ከፍ ማድረግ እንደሚገባ ሃሳብ ሰጥተዋል።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት በውይይቱ ላይ እንዳሉት ተቋሙ የምዝገባ ስርዓቱን ዲጂታላይዝ በማድረግ አሰራሩን ለማዘመን እንደተቋም የአምስት ዓመት ስትራቴጅክ እቅድ አውጥቶ እየሰራ ነው። 

በሃይማኖት ተቋማት  እና ጤና ተቋማት የሚከናወኑ የልደት፥ ሞት እና ሌሎች ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባን ተናባቢ እና ወጥነት ያለው እንዲሆን ትኩረት ሰጥቶ እየሰራም ነው ብለዋል።ተቋማቱ  ኩነቶችን ከማሳወቅ ባለፋ ውክልና ተሰጥቷቸው እንዲመዘግቡ እንዲሁም መረጃን አጠናቅረውና አደራጅተው እንዲልኩ ለማድረግ በትብብር እየተስራ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

 በምዝገባው ዙሪያ የአመራሩን ፥ መዝጋቢ አካላትን እንዲሁም የህብረተሰቡን ግንዛቤ ለማሳደግ ከመገናኛ ብዙሀን እና ከትምህርት ተቋማት ጋር በቅንጅት ይሰራልም ነው ያሉት ወይዘሮ ሰላማዊት።

የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ሳህረላ አብዱላሂ በበኩላቸው የሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ በሀገሪቱ  በመረጃ ላይ የተመሰረተ ለዜጎች ፍትሐዊ የጤና አገልግሎት ለመዘርጋት እንዲሁም በወሊድ ጊዜም ለእናቶች እና ህፃናት የጤና ክትትል ለማድረግ በተጨማሪም ሞትን ለመቀነስ አስፈላጊ በመሆኑ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

 የሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባን በተመለከተ የታወቀ፣ የተመዘገበና የዘመነ ማህበረሰብ ለመፍጠር  ከፌድራል እስከ ቀበሌ ወቅታዊ እና ጥራቱን በጠበቀ መልኩ ተግባራዊ እንዲሆን  መዝጋቢ፥ ባለድርሻ እና ተባባሪ አካላት በትብብር መስራት እንደሚገባቸው በፓናል ውይይቱ ላይ አቅጣጫ ተቀምጧል።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት

Latest Posts

Any Questions?

Call us!

8133