የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በኢትዮጵያ 8ኛዉን  የሲቪል ምዝገባ እና ቫይታል ስታቲስቲክስ ቀንን በመጪዉ ቅዳሜ ጥቅምት 1/2018 ዓ.ም በጅማ ከተማ እንደሚከበር ገለጸ።

አዲስ አበባ፡ መስከረም 9 ቀን 2018 ዓ.ም

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ከፍተኛ አመራሮች ለ8ኛ ጊዜ ጥቅምት 1/2018 ዓ.ም የሲቪል ምዝገባ እና ቫይታል ስታቲስቲክስ ቀን በዓልን ለማክበር ጅማ የገቡ ሲሆን የጅማ ከተማ ከንቲባ  አቶ ጠሃ ከመርን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የከተማው አመራሮች   አቀባበል  አድርገውላቸዋል።

የዘንድሮው የሲቪል ምዝገባ እና ቫይታል ስታቲስቲክስ ቀን “የሲቪል ምዝገባ ለዲጂታል የህዝብ መሰረተ ልማትና ለዲጂታል ህጋዊ መታወቂያ ስርዓቶች መሰረት ነው” በሚል መሪ ቃል  ነው የሚከበረው፡፡

ልደት፥ ጋብቻ ፥ ጉዲፈቻ ፥ ፍቺ እና ሞት አይነት የህይወት ወሳኝ ክስተቶችን እንዲሁም ቤተሰብን ማስመዝገብ ያለውን ፋይዳ በተመለከተ ህብረተሰቡን ለማስገንዘብ እና መነቃቃት ለመፍጠር በማሰብ ቀኑ በየአመቱ እንደሚከበር ነው የተገለፀው። 

የሲቪል ምዝገባ እና ቤተሰብ ምዝገባ ስርዓት በአስተማማኝ መልኩ ተግባራዊ እንዲሆን በመዝጋቢ አካላት እና ተባባሪ አካላት መካከል  ያለውን ትብብር ማጠናከር  ሌላው ቀኑን ለማክበር መነሻ መሆኑም ተገልጿል። 

 በ8ኛው የሲቪል ምዝገባ እና ቫይታል ስታቲስቲክስ ቀን በአል ላይ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላትን ጨምሮ ሌሎችም የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ አመራሮች፣ መዝጋቢና ባለድርሻ አካላት እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንደሚሳተፉ ይጠበቃል።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት

Latest Posts

Any Questions?

Call us!

8133