የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አዲስ ለተቀጠሩ 190 ሰራተኛች በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዩች ላይ ከግንቦት 4-9/2017 ዓ.ም ስልጠና መስጠት መጀመሩ ተገልፆል።





ለ3ኛ ዙር በአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ለ190 ሰራተኞች በሚሰጠው ስልጠና ተገኝተው የመክፈቻ ንግግርና የስራ መመሪያ የሰጡት የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት አገራዊ ለውጡን ተከትሎ ካለፈው ዓመት ጀምሮ 11 የሪፎርም አጀንዳዎቻችን እያከናወኑ እንደሆነ ገልፀዋል።
የመዋቅርና የደመወዝ ስኬል በመስራት የሰራተኛው ጥያቄ መመለስ እንደተቻለ ያብራሩት ዋና ዳይሬክተርዋ የተቋማችንን ሰፊ ኋላፊነት ለመወጣት ዘርፈ ብዙ ተግባራት እንደተከናወኑ ተናግረዋል።
አክለውም ከሰልጣኞች በሁሉም መንገድ ራሳችሁን ማዘጋጀት እና በስነ-ምግባር ማነፅ ይጠበቃል ብለዋል።
ሰልጣኞች በበኩላቸው የቅጥር ሂደቱ ግልጽ፣ ተደራሽና አሳታፊ እንዲሆን መደረጉን አመስግነው ቀጣይ አገር ተረካቢ ለመሆን ራሳቸውን ዝግጁ እንደሚያደርጉ ቃል እንገባለን ብለዋል።
