አዳማ፡ ግንቦት 15/2ዐ17 ዓ.ም
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ቢቂላ መዝገቡ በቀጣይ አዲሱን ቴክኖሎጅ ስራ ለማስጀመር እየተሰራ ያለውን የመሠረት ልማት ስራዎች ለመገምገም እና ያሉበትን ደረጃ ለማየት በአዳማ ቅርንጫፍ ድንገተኛ የስራ ጉብኝት አድርገዋል፡፡
በጉብኝታቸውም በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የሚሰጠውን የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደት ያዩ ሲሆን በቀጣይ አገልግሎት ፈላጊውን በተሻለ ደረጃ ለማስተናገድ እንዲቻል ቅ/ጽ/ቤቱን በመሠረተ ልማት እና ብቁ በሆነ የሰው ሀይል ለማደራጀት በሚቻሉባቸው ጉዳዬች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል፡፡
በውይይቱም ህብረተሠቡ ባለበት አካባቢ ፈጣንና ተደራሽ የሆነ አገልግሎት ለመስጠት የአገልግሎት ተቋሙ እየሰራ መሆኑን የገለፁት ም/ዋ/ዳይሬክተሩ በአዳማ ቅርንጫፍም የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት የሰው ሀይል ለማሟላትና ምቹ የስራ አካበቢ ለመፍጠር ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልፀው ሁሉም ሠራተኛ ህ/ሠቡን በቅንነትና በታማኝነት እንዲያገለግል እና ሀላፊነቱን እንዲወጣ አሳስበዋል፡፡
በመጨረሻም ለቅ/ጽ/ቤቱ አመራርና ሰራተኞች የስራ መመሪያና ትዕዘዝ በመስጠት ውይይቱ ተጠናቋል፡፡
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት
