የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት   የሲቪል ምዝገባ እና ቫይታል ስታቲስቲክስ ቀን ለ8ኛ ጊዜ በጅማ ከተማ እየተከበረ ነው። 

ጅማ፡ ጥቅምት 1 ቀን 2018 ዓ.ም

 የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት የሲቪል ምዝገባ ስርዓት በሃገሪቱ የሚገኙ ዜጎችን ከልደት እስከ ህልፈተ ህይወት የሚከሰቱ ክስተቶችን በመመዝገብና በማከማቸት መረጃ ማመንጨት ዋና ተግባር መሆኑን ጠቅሰው መረጃዎችም በዋነኛነት ለህግ፣ለአስተዳደርና ለስታትስቲክስ ፍጆታ ማዋል መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ተቋሙ ኢትዮጵያን የሚመጥንና ዘመኑን የሚዋጅ ዘመናዊ፣ ጥራቱንና ደረጃውን የጠበቀ ተደራሽ የሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ ስርአትን ማጠናከር የሚያስችል ከህግ፣ የአሰራር፣ የአደረጃጀት እንዲሁም በቴክኖሎጂ የማዘመን በርካታ ተግባራት በማከናወን ላይ ይገኛል ነው ያሉት።

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር በከር ሻሌ (ዶ/ር) ሲቪል ምዝገባና ቫይታል ስታቲስቲክስ መረጃ ስርዓት የሀገራችንን የ10 አመት የልማት ዕቅድ እና የአጀንዳ 2030 ዘላቂ የልማት ግቦች አፈጻጸምን ለመለካት ወሳኝ የመረጃ ምንጭ በመሆን ትልቅ ጠቀሜታ እንዳለው ገልፀዋል፡፡

የጤና ጥበቃ ሚንስትር ዴኤታ ወይዘሮ ሳህረላ አብዱላሂ የሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ ከመንግሥት የጤና እና ማህበራዊ አገልግሎቶች ለማግኘት ወሳኝ በመሆኑ ለምዝገባው ስኬታማነት ሁሉም አስተዋፅኦ ማበርከት አለበት ብለዋል።

የጅማ ከተማ ከንቲባ አቶ ጠሀ ቀመር  በበኩላቸው የሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ ለነዋሪ መታወቂያ ለመስጠት፣ የጋብቻ ህጋዊነትን ለማረጋገጥ፥ የመራጭነት ምዝገባ ለማካሄድ እና ሌሎች አስተዳደራዊ፥ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታዎች የጎላ መሆኑን በመገንዘብ ህብረተሰቡ በምዝገባው ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርግ ከተማ አስተዳደሩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

በበዓሉ ላይ  የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላትን ጨምሮ ሌሎችም የፌዴራልና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ አባ ገዳዎችና የሀገር ሽማግሌዎች፥ መዝጋቢና ባለድርሻ አካላት እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በመሳተፍ ላይ ናቸው።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት

Latest Posts

Any Questions?

Call us!

8133